Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች የጽዳትና የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የኮምፒውተር ቀለሞችና የደንብ ልብስ፣ የቢሮ ወንበሮች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት
- የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች
- የጽዳትና
- የጽህፈት መሳሪያዎች፤
- የኮምፒውተር ቀለሞችና
- የደንብ ልብስ፣
- የቢሮ ወንበሮች
በግልጽ ጨረታ ከ6211፡6212፡6218፡ 6219፡ 6313 በነጠለ ዋጋ አወዳድሮ መግዛትይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ኖሯቸው በገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ያላቸው በቫት የተመዘገቡና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚጫረቱበትን የእቃ ዓይነት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አሥር ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO) በወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበር የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ለፍርድ ቤቱ ዋናውን ማቅረብ አለባቸው ሆኖም አዲስ ከተደራጁ ውጪ ነባሮች ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አንድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: በዚሁ ቀን በ7:30 ተዘግቶ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡ ለተሸነፉት ተጫራቾች ወዲያውኑ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የእቃ ሳምፕል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከ1 ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በባለፈው ጨረታ አሸንፈው የአሸነፉበትን እቃ በተለያየ ምክንያት ለጽ/ቤታችን ማቅረብ ያልቻሉ በጨረታው አይሳትፋም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- መ/ቤቱ እቃዎቹን በብዛት የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ የወረዳው ፍርድ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡ አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃዎች በ30 የስራ ቀናቶች ውስጥ አጠናቀው ማስገባት አለባቸው፡፡
አድራሻ ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ሆለታ ከተማ ከአዲስ አበባ በአምቦ መስመር በ28 ኪ.ሜ. ላይ ይገኛል፡
ስልክ ቁጥር 011-237-05-30 /011-237 09 83/ 011 237-00-54
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ፍ/ቤት