Your cart is currently empty!
በላይአብ ሞተርስ ኃላ/የተ/የግል ማህበር የኪያ (KlA Spare parts) የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የመለዋወጫ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በላይአብ ሞተርስ ኃላ/የተ/የግል ማህበር የኪያ (KlA Spare parts) የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ።
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚቆየው ይህ በማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተከፍቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳሪስ ቀይመስቀል ወስጥ በሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን የመለዋወጫ ብዛት በተናጠል መጫረት ይችላል።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ሳሪስ ካዲስኮ ዋና መስሪያ ቤት የበላይአብ ሞተርስ ግቢ ውስጥ መውሰድ ይችላሉ።፡፡
ሞባይል፡– 0966-21-51-83/84
ስልክ ቁጥር፡– 011-4-34-36-91
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በላይአብ ሞተርስ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር