በምስራቅ ወለጋ ዞን የሌቃ ዱለቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሌቃ ዱለቻ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የጽህፈት፤ የፅዳት፤ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፤ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ፤ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ ሞተር ሳይክል፤ የክህሎት ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ወለጋ ዞን የሌቃ ዱለቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤትበ2018 በጀት ዓመት ለሌቃ ዱለቻ ሴክተር መስሪያቤቶች የጽህፈት፤ የፅዳት፤ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፤ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ፤ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ ሞተር ሳይክል፤ የክህሎት ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ዕቃዎች የመኪና ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፤

  1. ተጫራቾች በ2018ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር(ቲን)ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆንናቸውን ማስረጃ እና በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫት መጨመር አለባቸው፡፡ 
  3. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ለሌቃ ዱለቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ሙሉ በሙሉ ካስረከቡና ጥራቱ ከታየ በኋላ የሚከፈላቸው ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከሌቃ ዱለቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሰባቱንም ሆነ አንዱን ሎቶች የማይመለስ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ፤ስም፤ ፊርማ፤አድራሻና የንግድ ማህተማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡ 
  6. ተጫራቾች በአቅራቢነት ተርታ መመዝገባቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው በሁለት ፖስታ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በታሸገ በኤንቨሎፕ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8.  አሸናፊው ካሸነፉት አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ስምምነት ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገm CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የዋጋ ጭማሪ ሳይኖር ውሉን በማስረዘም ግዥውን 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  10. የሠራተኛ ደንብ ልብስን በተመለከተ ማለትም ጨርቅ ፖስታው ታሽጎ ሲመለስ ከፖስታው ጋር ናሙናው የሚቀርብ ሲሆን የሚቀርቡ ዕቃዎች በሙሉ በተጠቃሚዎች ከታዩ በኋላ ርክክብ የሚደረግ ይሆናል ::
  11. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ /CPO/10,000/አስር ሺህ/ ከጨታረው መወዳደሪያ ኦርጅናል አንድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ተጫራቾች ሆኑ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ባይገኙም ጨረታው ለመከፈት የሚያግድ ነገር ሊኖር አይችልም::
  13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴን ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  14. ጨረታው በጋዜጣ፣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለበለጠ መረጃ +2519 34 39 2199/+2519 35 88 6718/+251 920 410 808 /+2519 840 28841/251917 63 77 49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የምሥራቅ ወለጋ ዞን የሌቃ ዱለቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት