Your cart is currently empty!
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት ለክ/ከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ፈርኒቸሮች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት ለክ/ከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የፅህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፤ ፈርኒቸሮች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
የጨረታ መመሪያ፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ Tin ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በአቅራቢዎች ዝርዘር የተመዘገቡና ግብር መክፈሉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክከል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
- ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት፡ ተጫራቾች የቀረበውን እስፔስፊኬሽን በመተው ዋጋ ሞልተው ቢገኙ ባቀረብነው እስፔስፊኬሽን እንደተሞላ ሆኖ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ናሙና የተጠየቀባቸውን እቃዎች እንደ የደንብ ልብስ፡ ኤሌክትሮኒክስ እና የጽዳት እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ በ10 (አስር) ቀን ውስጥ ውል መግባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው የጨረታው ውጤት ተገልጾ እስከ 5( አምስት)ቀን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ቀን በኋላ የመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ለሁሉም እቃዎች ቫትን (VAT) ጨምሮ መሙላት እና አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን የእቃ አይነቶች እስከ መስሪያ ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ (price Validity date) ከጨረታው መክፈቻ እለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበትን ጊዜ (delivery time) መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- ሱሉልታ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መረዳት ይችላሉ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx