Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ቋሚ እቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ የጽዳት እቃ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የመኪና እቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና የመኪና ዘይቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን
- ሎት 1 ቋሚ እቃ
- ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃ
- ሎት 3 የጽዳት እቃ
- ሎት 4 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 5 ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የመኪና እቃዎች
- ሎት 6 የመኪና ጎማ
- ሎት 7 የመኪና ዘይቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በ16/12/2017 የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፍኬት ያላቸው።
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ / በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-7 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-7 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 20 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት በመክፈል ከ16/12/2017 ዓ.ም እስከ 30/12/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በየሎቱ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት 16/12/2017 ዓ.ም እስከ 30/12/2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በቀን 1/13/2017 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ይሁን እንጅ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪው መስሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ቀን ከ 5 /አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913509999 ወይም 0904662494 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል፤ ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ60 ቀናት ይሆናል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፉ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል።
- ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% ( ሃያ በመቶ ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Fuel and Lubricants cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, Electromechanical and Electronics cttx