በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር ግማ 001/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተለያዩ ምድብ (ሎት) የተከፋፈሉትን ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፦

ምድብ ሎት

የዕቃው/አገልግሎት አይነት

 

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ

የጨረታ ማስከበሪያ

 

ምድብ 01

የሰራተኞች ደንብ ልብስ

 

ብር 100.00

 

ከጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ

ምድብ 02

ልዩ ልዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽህፈት መሳሪያዎች

ብር 200.00

 

ከጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ

ምድብ 03

የተለያዩ ህትመቶች

ብር 100.00

ከጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ

ምድብ 04

ለቢሮ ጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች

ብር 100.00

ከጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ

ምድብ 05

የተሽከርካሪ ጌጣጌጦች እና ሌሎች የተሽከርካሪ አላቂ ዕቃዎች

ብር 100.00

ከጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ

ምድብ 06

የተለያዩ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎችና የአይ ዕቃዎች

ብር 200.00

 

ከጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ

 ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዝርዝር መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ ከዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው ከሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
  3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT 15%) ተመዝጋቢ የሆነ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበና ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ .. በማቅረብ 10 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም የሚችል፣
  4. ለምድብ (ሎት) 01 የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ ለምድብ (ሎት) 02 ልዩ ልዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ለምድብ(ሎት) 03 የተለያዩ ህትመቶች ለምድብ (ሎት) 04 ለቢሮ ጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች እና በምድብ (ሎት) 05 የተሽከርካሪጌጣጌጦች እና ሌሎች የተሸከርካሪ አላቂ ዕቃዎች ላይ ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቅድሚያናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትርበሥራ ሰአት (ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር) በአዲስ አበባ ከተማ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ቢሮ 3 ወለል በመገኘት የጨረታ ሰነዱንከላይ በሰንጠረዥ በየሎቱ በተቀመጠው የብር መጠን በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
  6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ሰነድ) ኦርጅናልና ኮፒ፣ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት ለየብቻውበፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማኅተምና ፊርማ በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የመንግስት ግዥንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ 3 ወለል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፣
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለ ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ላይ ጨረታው ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ሕዝባዊ ወይም ኃይማኖታዊ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜ እና እሁድከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች በጨረታው አከፋፈት ስርዓት ላይ በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው አይስተጓጎልም፣
  9. ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ በጨረታው ላይ ቅሬታ ካለው ለመ/ቤቱ የበላይ አካል አቤቱታ ማቅረብ ይችላል።
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ መስከረም ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው ቴሌ ጋራጅ አካባቢ ከሚገኘው ካሮጋ ፋርማ ህንፃ (የዱሮ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢሮ) የመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ 3 ወለል ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 126 3693 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን