Your cart is currently empty!
በወላይታ ልማት ማህበር የጉታራ ሆቴል ቱሪዝምና ሥልጠና ማዕከል High Quality Imported plastic cafeteria chair በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በወላይታ ልማት ማህበር የጉታራ ሆቴል ቱሪዝምና ሥልጠና ማዕከል High Quality Imported plastic cafeteria chair በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ መፈጸም ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት ማቅረብ ያለባቸው፡–
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- የተፈለጉትን ዕቃዎችን በተፈለገው ዓይነት እና ሞዴል ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ) ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/ አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ገዳም ሰፈር በሚገኘው በወላይታ ልማት ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የዕቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመግዛት አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው በታሸገ ፖስታ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በሚቀጥለው በሚውለው በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም።
- ሆቴሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፤
በስልክ ቁጥር 0461802970 / 0465515128 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ገዳም ሰፈር በሚገኘው በወላይታ ልማት ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በወላይታ ልማት ማህበር የጉታራ ሆቴል ቱሪዝምና ሥልጠና ማዕከል