Your cart is currently empty!
የምስራቅ ወለጋ ዞን ጅማ አርጆ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉት የመንግስት መ/ቤቶች ለ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል አላቂ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና ጎማ፣ የሞተር ሳይክል ጎማ፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤ የግንባታ ዕቃዎች፣ የቴክኒክ (የሥልጠና) መሣሪያዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ወለጋ ዞን ጅማ አርጆ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉት የመንግስት መ/ቤቶች ለ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል አላቂ ዕቃዎች፡- የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ የመኪና ጎማ፣ የሞተር ሳይክል ጎማ፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤ የግንባታ ዕቃዎች የቴክኒክ (የሥልጠና) መሣሪያዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የ2017/18 የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ከጅማ አርጆ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሠራተኛ ደንብ ልብስ በተመለከተ ከጨረታ ሰነድ ጋር የተወዳደሩትን ዋጋ ሲሞሉ ናሙናውን በፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ በናሙና መሠረት ጥራት የሌለውና ደረጃውን ያልጠበቀ ከሆነ ወዲያውኑ ይዘው ይመለሳሉ፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር ዋጋ መስጫ ላይ ሲሞሉ በተጠየቀው specification መሠረት ሆኖ ዋጋውን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጭምር በመሙላት ሙሉ አድራሻቸውን ስምና ፊርማቸውን፤ ማወዳደሪያ ቅጽ ላይ በማድረግ ሙሉ ዶክሜንታቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ በቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው ሣጥን ጨረታው ከመዘጋቱ እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፣
- የጨረታው ሣጥን ከታሽገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
- የጨረታ አሸናፊ በራሱ ወጪ ዕቃዎቹን በወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ አድርጎ ገንዘቡን ይቀበላል፡፡
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የዋጋ ጭማሪ ሳይኖር ውሉን በማስረዘም ግዥውን 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ከማምጣታቸው በፊት በአካል ቀርቦ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ውል መፈጸም ይኖርባቸዋል፣፣
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ15ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 09 17 09 30 02/ 09 27 50 07 00/ 09 17 56 92 6/09 17 28 87 48
የምስራቅ ወለጋ ዞን የጅማ አርጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Textile, cttx Tri Wheeler, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Motorcycles and Bicycles Purchase cttx