Your cart is currently empty!
የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል ለዶሮ መኖነት የሚውል አንደኛ እና ጥራቱን የጠበቀ ወቅታዊ ምርት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
- ፉሩሽካ
- ፉርሽኬሎ
- አኩሪ አተር
- የኑግ ፋጉሎ
- እስታርተር ፕሪሚክስ
- ሌየር ፕሪሚስስ
- ላዮሲን
- ሚቶኒን ከላይ የተገለጹት ምርት የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል በመራባት ላይ ላሉ ዶሮ መኖነት የሚውል አንደኛ እና ጥራቱን የጠበቀ ወቅታዊ ምርት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዘርፉ የተሠማራችሁ ነጋዴዎች፡–
- ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው እና ማዕከሉ በሚፈልገው መጠንና ጥራት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው የጨረታ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ካሁን ቀደም በመሳሳይ ሥራ የተሻለ አፈፃፀም ያለው፤ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እና ኦርጂናል በማቅረብ አመሳክሮ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የተሟላ ሠነድ ለየብቻ 1/አንድ/ኦሪጂናል 2. ሁለት ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በኦሪጂናል 50,000/ሃምሳ ሺ ብር /CPO/ የተያዘበት ሠነድ ገብቶ መታሸግ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ በደቡብ ምዕራቡ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ቦንጋ ዶሮ እርባታ አካውንት ቁጥር 1000029079987 ላይ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ከቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ22ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል በኩል ይከፍታል።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀ ቦታና ሰዓት የመዝጊያና መክፈቻ ቀን ይሆናል።
- የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
- ተጫራቾች በሚያቀረቡት ማንኛውም ኦሪጂናል መረጃ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል።
- የጨረታው አሸናፊ በ7 ቀናት ውስጥ ውል ገብቶ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል።
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ 047 331 0841/ 09 34 44 98 83 ላይ ደውለው ይጠይቁ።
የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል