የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2018 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጫዋቾችን በሆቴል ለመመገብ እና የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመገልገል እና ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2018 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጫዋቾችን በሆቴል ለመመገብ እና የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመገልገል እና ለመግዛት ይፈልጋል

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት የምትችሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ እየጋበዝን፡-

  1. በየዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. አሸናፊው ድርጅት ለመልካም የሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡
  4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን እንድትገዙ እየገለጽን እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ መግለጫውን በማያሻማ መልኩ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በመሙላት ሁሉም የጨረታ ሰነዶች ኦሪጅናልና ኮፒ በድምሩ 2 ፖስታዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከፊትና ጀርባው ላይ የድርጅቱን ማህተምና የባለቤትነት ፈርማ በማድረግ በእናት ፖስታ ውስጥ ተጨምሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ቅዳሜና እሁድን ያካተተ ይሆናል፡፡
  5. የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. በጨረታው ያሸነፈ ተወዳዳሪ የባለሙያ አስተያየት ላይ መሠረት በማድረግ ውል ገብቶ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፤ ሁሉም ተጫራች አድራሻውንና ቦታውን እንዲሁም የስልክ ቁጥር መግለጽ ይኖርበታል፡፡ በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. የእያንዳንዱ ግዥ መጠን በሽያጭ ሠነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ሃያ በመቶ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡
  8. መ/ቤቱ የዕቃው ጥራት በባለሙያና በስፖርተኞች ሲረጋገጥ ብቻ ውል ተዋውሎ ማስቀጠል የሚቻል ይሆናል፡፡
  9. በጨረታው ማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለጹ ካሉ እንደ ማስታወቂያው የሚያገለግል ስለሆነ ሁሉም ተጫራች ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል፡፡
  10. ክለብ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ሲሆን በዕለቱ በ9፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ሆኖ በዕለቱ በ9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የማይገኙ ከሆነ የጽ/ቤቱን ስራ አያስተጓጎልም፡፡ የተጫራቹ ተወካይ የሚቀርብ ከሆነ ስለ ውክልናው ህጋዊነት የሚገልጽ መረጃ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
  12. የክለብ ጽ/ቤቱ አድራሻ በአ/ምንጭ ሁለገብ ስታዲየም የሚገኝ ሲሆን ለበለጠ መረጃ በ 046-881-3605/ 09-16-87-84-22) ይደውሉ፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *