የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን በቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/08/WM/2018

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን በቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። 

ስለዚህ የሚ ከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብረ ከፋይነት መለያ ቁጥር፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት)ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁም ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በቦኬ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግስት መ/ቤትየሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  6. ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እሰከ 09/1/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው እስከ 09/1/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት በቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 2 ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፤ ጨረታው በዚሁ እለት ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  9. አሸናፊ ድርጅት ተጫራቹ ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ቦኬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  10. ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  11. በሽያጭ የቀረበው ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ነጋዴው አሸናፊ ድርጅቱ/በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት።
  12. የዕቃውን ማስጫኛና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፐ ውስጥ አድርገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  14. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻችን፡- በቦኬወረዳ ገ/ጽ/ቤት

ቦኬ ጢቆ

ሞባይል-09-21-66-18-39/09-11-36-98-61

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን የቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *