Your cart is currently empty!
የደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ መንግስት የሸካ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ መንግስት የሸካ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን ለመፈጸም ከዚህ በታች ያሉ መስፈርቶችን የሚያማሉ ድርጀቶችን ለጨረታ ይጋብዛል።
በዚሁ መሠረት የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘርፉ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና በአገልግሎት አቅራቢ ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ድርጅቶችን ይጋብዛል።
- የተዘረዘሩ መስፈርቶች ካሟሉት መካከል ጥረቱን የጠበቀ እና ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውን በመምረጥ አሸናፊው ይለያል።
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው, በተገኙበት ሠነዱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናስታውቃለን።
- ተጫራቸች የጨረታውን ሰነድ ከሸካ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በወኪሎቻቸው አማካኝነት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከማንኛውም በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ በጥሬ ብር ለእያንዳንዱ 5,000 /አምስት ሺህ/ ብር ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበት ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒውን በመለየት በማሸግ እንዲሁም የድርጀቱን ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ በሚፈልገውን የጥራት ደረጃ የጠበቀና በእስፔስፊኬሽን መሠረት ካላቀረበ በመንግስት ህግና ደንብ መሰረት መ/ቤቱ በህግ አንዲጠየቅ ያደረጋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊዎች እቃዎቹን በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ያደርሳሉ።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 047-5-58-00-31 እና 09-45-65 08-96 ላይ ይደውሉ።
በደ/ምዕ/ት/ህ/ክ/መንግስት
የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት