የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች ከ20/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሀራጅ ጨረታ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ለሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል።
  5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ዕቃ ክፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት።
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲፒኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  8. በጨረታው ያሳሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል።
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀን ገደብ መሸኛ ሲሰጣቸው ይችላል። 
  11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
  12. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 20/12/2017 ዓ.ም ከ2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ22/12/2017 ዓ.ም በ3:45 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በ22/12/2017 ዓ.ም በ4፡15 ሰዓት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።

N.B: አሸናፊው ተጫራቾ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕስ ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀሳፊነቱን አይወስድም።

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት