የፈለገ ብርሃን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳደሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2017

የፈለገ ብርሃን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመደበኛ በጀት

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ 4000.00 ብር
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት 2000.00
  • ሎት 3 አላቂ የፅዳት ዕቃ 4000.00
  • ሎት 4 የፕላንት ማሽነሪ ዕድሳት 2000.00
  • ሎት 5 አላቂ የቢሮ ዕቃ 3000.00
  • ሎት 6 ቋሚ ዕቃ 5000.00 ብር
  • ሎት 7 አላቂ የትምህርት ዕቃ 3000.00
  • ሎት 8 የህትመት ስራ ሎት 1000.00
  • 9 የመስተንግዶ ግብአት 2000.00
  • ሎት 10 የሽልማት ዕቃ 3000.00
  • ሎት 11 የተለያዩ የጥገና ስራ 3000.00
  • ሎት 12 10,000.00 የት/ቤቱ ክበብ ኪራይ ሲፒኦ ከሚያሲዙ ድርጅቶች በጨረታ አወዳደሮ መግዛትና ማስራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታ መሣተፍ የምትፈልጉ ተጨራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።

  1. ተጫራቾች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  2. 2017 . የታደሰ ንግድ ፍቃድና ክሪላንስ የታደሰ በተሰጣቸው ንግድ ዘርፍ ብቻ መሣተፍ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ብር 42,000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባችኋል
  5. ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ከት/ቤት ፋይናንስ ክፍል በግንባር ቀርበው ወይም ህጋዊ ወኪል አማካኝነት በብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር በመክፈል መግዛት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  7. ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዶችን ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይሆናል።
  10. ውል ማስከበሪያ ስትዋዋሉ 10% እንድታሲዙ
  11. የት/ቤቱ ክበብ የቤት ኪራይ መብራት ውሃ በነፃ በተጨማሪ እንጀራ እዛው ጊቢ ውስጥ እንዲጋገር
  12. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ጥቃቅንና ነስተኛ ተወዳዳሪዎች በምታመርቱት ምርት ብቻ ነው መወዳደር የምትችሉት።
  14. አቅራቢዎች ላሸነፋችሁበት እቃ በራሳችሁ ትራንስፖርት /ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  15. 1ተጫራቾች የገዙትን የግዥ ሰነድ በትክክል ሞልተውና ማህተማቸውን አድርገው መመለስ አለባቸው
  • አድራሻ ጎጃም በረንዳ ከወለጋ ሆቴል ወደ ሩፋኤል በሚወስደው መንገድ ላይ ጨው በረንዳ ፊትለፊት ካለው አዲስ ህንፃ ወደ ውስጥ በግምት 50 ሜትር ገባ ብሎ

ለበለጠ መረጃ፡ስልክ ቁጥር 011-2-73-32-42

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት

የፈለገ ብርሀን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት