ቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃ፣ አላቂ የህትመት እቃዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎችና አላቂ የማስተማሪያ እቃዎች፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የጥገና እቃዎች እና ቋሚ እቃዎች የግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር -001/2018 ዓ.ም

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 የሚገኘው ቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት አመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ማለትም

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ 
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃ፣
  • ሎት 3 አላቂ የህትመት እቃዎች፣
  • ሎት 4 አላቂ የህክምና እቃዎች
  • ሎትና 5 አላቂ የማስተማሪያ እቃዎች 
  • ሎት 6 አላቂ የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
  • ሎት 8 የጥገና እቃዎች
  • ሎት 9 ቋሚ እቃዎች

 ብቃት ካላቸው እና በመስኩ ከተሰማሩ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል ፡፡

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በባንክ የተረጋገጠ CPO ሰቆጣሪ /የመ/ደ/ት/ቤት ተብሎ በማዘጋጀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ CPO ለማያሰሩ ማህበራት ከአዳራጃቸው አካል በት/ቤታችን ስም የዋስትና ደብዳቤ እና የምስከር ወረቀት እንዲሁም ጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ከሲራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ከታች በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ሎት 1 የደንብ ልብስ ብር 21000.00፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 5250.00 ፣ ሎት 3 አላቂ ህትመት እቃዎች ብር 2100.00፣ ሎት 4 አላቂ የህክምና ኢቃዎች ብር 315.00 ፣ ሎት 5 የማስተማርያ እቃዎች ብር 12603.54፣ ሎት 6 አላቂ የፅዳት እቃዎች ብር 19870.20፣ ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 15750.00፣ሎት 8. የጥገና እቃዎች ብር 15750.00 ፣ ሎት 9. ቋሚ እቃዎች ብር 10500.00
  4. ተጫራቾች በተወዳደሩባቸው ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ናሙና ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሎት 9 ት/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ ብቻ ቫትን ጨምሮ ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ዋጋውን ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በፋይናንስ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰአት በት/ቤቱ ፋ/ቢሮ ይከፈታል።
  8. የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ይከፈታል
  9. የዘገየ ተጫራችና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ አድራሻ – ን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 11 ወረድ ብሎ ሰኞ ስሙ ሀና

ቀለበት ቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት ክልል አ.አ የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡- 011-471-1190

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11

ት/ጽ/ቤት ቆጣሪ የአንደኛ / ደ/ ት / ቤት