በሸገር ከተማ አስተዳደር በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ የዳለቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የሰራተኛ ደንብ ልብሶች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች እና የመኪና ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

በሸገር ከተማ አስተዳደር በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ የዳለቲ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ለወረዳው ሴክተር /ቤቶች ለማዘጋጃ ቤቱ 2018 በጀት ዓመት የሚውሉ

  • የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  • የሰራተኛ ደንብ ልብሶች፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች፤
  • የቢሮ ፈርኒቸሮች እና የመኪና ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ዝርዝር ሁኔታዎች፡

የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የዳለቲ ወረዳ ገንዘብ /ቤት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1065015371216 ገቢ በማድረግ deposit silp በመያዝ ከዳለቲ ወረዳው ገንዘብ /ቤት የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት ሂደት ክፍል ሰነዱን መግዛት ይችላል።

የተጫራቾች ግዴታዎች፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፡፡ እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) 15,000 ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ግዴታ አለባቸው:: የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት 2017 የተደራጁ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በመጥቀስ ካደራጃው /ቤት በቀጥታ ለመ/ቤታችን በኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ በማጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ (ከወረዳ የሚጻፍ ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም)።
  5. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ዕቃዎችን በራሳችሁ ወጪ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  6. አሸናፊ የሆነ ተጫራች ውል ሊፈርም ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የስራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 400 ሰዓት አድራሻ በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ዳለቲ ገንዘብ /ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች ከጠየቁበት ዕቃዎች ላይ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው 16ኛው ቀን ከቀኑ 400 ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-22-73 76-12/09 -13 -89 60-75 በመደወል መረዳት ይችላሉ።

በሸገር ከተማ አስተዳደር በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ

የዳለቲ ወረዳ ገንዘብ /ቤት

ዳለቲ