በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ስር የሚገኘው የልቤ ፋና ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 የበጀት ዓመት የግንባታ ስራዎች እና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ስር የሚገኘው የልቤ ፋና ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች ያሉትን የግንባታ ስራዎች እና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 – የግንባታ ስራ
  • ሎት 2 – የደንብ ልብስ
  • ሎት 3- የጽህፈት እና የቢሮ መሳሪያዎች
  • ሎት 4- የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 5 ማጣቀሻ መጻሕፍቶች
  • ሎት 6- ህትመት
  • ሎት 7- የፎቶ ኮፒ እና የፕሪንተር የጀስትነር ጥገና ስራዎች

ተጫራቾች ማሟላት ያስባቸው፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
  4. በአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው
  5. ናሙና ለሚጠይቁ ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸሁ።
  6. አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. በግንባታ ዘርፉ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጥሩ የአፈፃፀም ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO በየሎቱ የሚቀርብ ሲሆን
  • ለግንባታ ስራ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 CPO ማሰራት አለባችሁ
  • ከሎት 2 እስከ ሎት 7 ያሉት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 CPO ማሰራት አለባችሁ

9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በመሙላት ዘወትር በሥራ ቀናት በስራ ሰዓት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

10. የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናሉ ለብቻ እና ኮፒው ለብቻ ተለይቶ በሁለት በተለያዩ ፓስታዎች ታሽጎ መቅረብ አለበት።

11. የሚከፈተው ኮፒው ስለሆነ ማንኛውም ማስረጃ ለምሳሌ ሲፒኦ፣ ንግድ ፈቃድ የመሳሰሉት ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተጨምሮ መመለስ አለበት።

12. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ካላቀረቡ በጨረታው የማይሳተፉ መሆኑን እናሳውቃለን ።

13. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ 400 ብር በመክፈል ሰነዱ መውሰድ ይችላሉ።

14. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የግንባታ ስራው በተጨማሪም ከሎት 2- ሎት 7 ድረስ ያለው ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይዘዋወራል።

15. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ካዛንቺስ ንግድ ባንክ ወረድ ብሎ የልቤ ፋና ቅድመ አንደኛ አንደኛና መከከስኛ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-551-8669 ይደውሉ።

በቂርቆስ ክ/ከተማ የልቤ ፋና ቅ/አንደኛ፣ አ/መካ/ደ/ት/ቤት