በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ሸዋ ዞን የመተሃራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች ለ2018 ዓ/ም የበጀት ዘመን የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ሸዋ ዞን የመተሃራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች ለ2018 ዓ/ም የበጀት ዘመን በአዲሱ የመንግስት የግዢ መዋቅር የሥራ ሂደት መሠረት ግዢ ለመፈጸም እና በሥራ ላይ በማዋል አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ማለትም፡-

  1. የጽዳት እቃዎች
  2. የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች እና ጠረፔዛዎች
  3. የሠራተኛ የደንብ ልብስ
  4. የጽሕፈት መሳሪያዎች
  5. ኮምፒውተሮችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  6. ሞተር ሳይክሎች ሲሆኑ

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያማሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ከላይ 1-6 የተጠቀሱትን እቃዎች አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) የመተሃራ ከታማ ገንዘብ ጽ/ቤት 107060632114 ስንቄ ባንክ ገቢ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
  2. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በመተሀራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
  3. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 022 226 0649 ይደውሉ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምሥራቅ ሸዋ ዞን የመተሃራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት