በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ፈርኒቸር (ቋሚ ዕቃዎች)፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ቋሚ ዕቃዎች) እና የደንብ ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ  /ቤት 2018 በጀት ዓመት ለሴክተር /ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ፡

  • የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች
  • የመኪና ጎማዎች
  • ፈርኒቸር (ቋሚ ዕቃዎች)
  • ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ቋሚ ዕቃዎች)
  • የደንብ ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ /መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  2. የአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ አምስት መቶ) ብር በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን /ቤት በመክፈል ሰነዱን ከኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ /ቤት መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ /ቤት በተዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
  5. ጨረታው 16ኛው ቀን 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ (ተዘግቶ) በዚሁ ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ /ቤት ውስጥ ይከፈታል፤ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መሰረት የተጫረተበትን ዕቃ ናሙና /Sample/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
  10. ጥራት (Quality) በሌላቸው እቃዎች ላይ (በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች ከተሰጠ መስፈርት (Standard) በታች የሚያቀርብ ተጫራች) መስሪያ ቤቱ የማይደራደር መሆኑን በቅድሚያ እናሳውቃለን።
  11. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም።
  12. /ቤታችን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈለጊነቱ እስከ (20%) በመጨመር ወይም በመቀነስ መግዛት ይችላል።
  13. መወዳደሪያው በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶመቅረብ ይኖርበታል።
  14. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011439-94 93 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር

የኮዬ ፈጬ ክፍ ከተማ ገንዘብ /ቤት