Your cart is currently empty!
የቀጨኔ ደብረ ሰላም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማስጠገን ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-001/2017 ዓ.ም.
የቀጨኔ ደብረ ሰላም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም በመደበኛ እና ከውስጥ ገቢ በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማስጠገን ይፈልጋል።
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ (ሎት 01)፤
- የቢሮ እቃዎች (ሎት 02 )፤
- አላቂ የትምህርት እቃዎች (ሎት 03)፤
- የፅዳት እቃዎች (ሎት 04)፤
- የጥገና ዕቃዎች (ሎት 05)፤
- ቋሚ ዕቃዎች(ሎት 06)፤
- የህትመት ዕቃዎች (ሎት 07)፤
- የማሽነሪ ጥገና (ሎት o8)፤
- መፅሐፍት(ሎት 09)፤
- የመኪና ኪራይ (10)፤
- የመኪና ጥገና (11)፤
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸዉ መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከብር 50,000 ሺህ በላይ ለሚወዳደሩ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማናቸውም ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀመሮ ባሉት 10/አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በሥራ ሰዓት በፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚውዳደሩበት ዋጋ ኮፒ እና ኦርጅናል በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ናሙናዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ያልቀረበ ዕቃ የማይወዳደር ሲሆን ግን የተሟላ ናሙና በአካል ማቅረብ የማይችሉ ሲሆንና የማይችሉበትን ምክንያት የመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ሲቀበለው ስለናሙናው ያላቸውን መረጃ በፎቶ ግራፍ መልክ ማቅረብ እንዲችሉ ሊፈቅድ ይችላል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የሥራ ቀን በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን በ2፡30 ሰዓት በቀጨኔ ደብረ ሰላም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፋይናንስና ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው ለዓመቱ ግዥ የተያዘ በጀት መሰረት በማድረግ ለደንብ ልብስ 12000′ ለቢሮ ዕቃዎች 17000 ለትምህርት ዕቃዎች 7200′ ቋሚ ዕቃዎች 9221.12′ ለጥገና ዕቃዎች 2000/ ህትመት 1000ብር/መጽሐፍት=600/ለፅዳት እቃዎች/15000//ማሽነሪ ፅገና፤2000/የመኪና ኪራይ፤500/የመኪና ጥገና፤5000 ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚመጣ የጨረታ ማስከበሪያም ሆነ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስረከብ ይኖርበታል።
- መሥሪያ ቤቱ የጠቅላላ የዕቃው ብዛት ላይ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
- ውል ከተዋዋሉ በኋላ ከአንድ እቃ ላይ 25% መጨመር ይቻላል።
- ጥቃቅን አና አነስተኛ ተጫራቾች አምራች በሆኑበት የሥራ ዘርፍ ብቻ መወዳደር ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ፡– ከቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ከኢትዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ መርሲ ኬር ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡– 011-1-57-45-52/ 011-1 56-76 65/ 011-8-69 61-70 በቀጨኔ ደብረ ሰላም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፋይናንስና ግዥና ንብረት አስተዳደር በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
አድራሻ፡– በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የቀጨኔ ደብረ ሰላም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከቀጨኔ
አካል ማቅረብ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን 200 ሜትር ገባ ብሎ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የቀጨኔ ደብረ ሰላም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Hospitality, cttx IT and Telecom cttx, cttx Machinery cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Rent cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, cttx Tour and Travel cttx, cttx Vehicle (garage service) cttx, cttx Warehousing, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Tour and Travel cttx, Transit and Transport Service cttx