የቱሉቦሎ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ ለሥልጠና የሚውሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን፣ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ብትን የደንብ ልብሶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የግንባታ መሳሪያዎችን፣ የፈርኒቸር፣ መለዋወጫ ዕቃዎችን፣ የመካኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018

የቱሉቦሎ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ ለሥልጠና የሚውሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን፣ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ብትን የደንብ ልብሶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የግንባታ መሳሪያዎችን፣ የፈርኒቸር፣ መለዋወጫ ዕቃዎችን፣ የመካኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ስመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ፦

  1. የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)፣ የአቅራቢነት ማስረጃ እና VAT ተመዝጋቢ ከሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. የዕቃዎችን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታይ የስራ ቀናት በደ/ምዕ/ሸዋ በበቾ ወረዳ ቱሉቦሎ ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 1 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  4. የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው ቦታ ይከፈታል።
  6. አስራ አንደኛው ቀን ዝግ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  7. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀ ቀን ጀምሮ እስከ 10 ባሉት ቀናት በበቾ ወረዳ ቱሉቦሎ ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ቱሉ ቦሎ ከተማ ከኢአ 80 ኪሎ ሜትር በጅማ መንገድ ላይ በራሳቸው መጓጓዣ ዕቃዎችን አቅርበው ማስረከብ አለባቸው።
  8. አሸናፊው በጨረታው መሰረት ዕቃዎችን በሙሉ ሲያስረክብ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸምለታል።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር 011 342-0850/ 011 342-1020
በኦሮሚያ ስራ ዕድል ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ የቱሉቦሎ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ