Your cart is currently empty!
የነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለነጌሌ አርሲ ከተማ ለመንግስት መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ 01/2018
የነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለነጌሌ አርሲ ከተማ ለመንግስት መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት በ1ኛ ዙር ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት አንድ (1) – የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች፤
- ሎት ሁለት (2) – አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፤
- ሉት ሶስት (3) – የቢሮ የጽዳት እቃዎች፤
- ሎት አራት (4) – የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች
- ሎት አምስት (5) – ቋሚ የቢሮ እቃዎች (ፍርኒቸሮች)
- ሎት ስድስት (6) – የቀላል እና ከባድ መኪና ጎማዎች
- ሎት ሰባት (7) – ሞተር ሳይክል
- ሎት ስምንት (8) – የደንብ ልብስ
ስለዚህ ዕጩ ተጫራቾች ሊያውቁት የሚገባቸው መመሪያ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡ እና ሕጋዊ የሆነ የታደሰ የ2017/2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN No.) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የግብር ከፋይነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- መስሪያ ቤታችን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT 15%) 50%ቱን ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን እናስውቃለን።
- እያንዳንዱ ተጫራች ከላይ በየሎቱ ለተዘረዘሩት እቃዎች በየሎቱ በተጠቀሰው መሰረት ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች ብቻ ለብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የኢትዮጵያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች CPO ጋራ ማስያዝ አለባቸው። አዲስ የማይክሮ ድርጅቶች ኦሪጅናል የዋስትና ደብዳቤ በህጋዊነት ካደራጃቸው አካል ማቅረብ አለባቸው። የዋስትና ደብዳቤው የሚያገለግለው አዲስ ለተደራጁ ማይክሮዎች ብቻ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።
- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ፖስታዎች ላይ የሚወዳደሩባቸውን ሎቶች ቁጥራቸውን እና አይነታቸውን መፃፍ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በየሎቱ ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ለየብቻ ወይንም በተናጠል የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የስራ ቀን 15 (አስራ አምስት) ቀናት ነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ዋጋ ቦታ በነጠላ ዋጋ መግለፅ እና በጥንቃቄ ቫትን (VAT 15%) ጨምሮ በመሙላት ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ በታሸጉ ፖስታዎች ውስጥ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በነጌሌ አርሲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ክፍል ይከፈታል። ካልተገኙም ጨረታው አይደናቀፍም። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን፣ ስማቸውንና አድራሻቸውን በግልጽ መጻፍ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማሳረፍ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ4 ቀናት ውስጥ በነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ ካሸነፈው ዕቃ ላይ አስር ፐርሰንት /10%/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የዕቃዎቹን ናሙና በመያዝ ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል።
- በተራ ቁጥር 11 ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ውል የማይፈጽም አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ በማድረግ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።
- አሸናፊው ተጫራች የሸነፈባቸውን ዕቃዎች ውል ተፈራርሞ እስከ 15 /አስራ አምስት/ ቀን ከላይ በተገለጸው አድራሻ በራሳቸው መጓጓዣ ዕቃዎቹን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ላይ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ለስልሳ) ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ የነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ
- ቁጥር 09-16-00-03-22/ 09-16-04-42-13 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Textile, cttx Tri Wheeler, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Motorcycles and Bicycles Purchase cttx