የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 001/2018

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ 13,000.00
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 6,000.00
  • ሎት 3 ህትመት. 2,000.00
  • ሎት 4 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች.29,000.00
  • ሎት 5 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 13,000.00
  • ሎት 6 ፕሪንተር እና ሌሎች ተዛማጅ ኤሌክትሮኒክስ 12,000.00
  • ሎት 7 ፈርኒቸር የቤትና የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች 4000.00
  • ሎት 8 የቀይ መስቀል ዕቃዎች, 2,000.00
  • ሎት 9 ልዩ ልዩ ኬሚካሎች.  2,000.00
  • ሎት 10 ነዳጅና ቅባት. 2,000.00
  • ሎት11 ኤሌክትሮኒክስ እድሳትና ጥገና. 3,000.00
  1. በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ።
  2. በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገበበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ማስገባት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበርያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ለየአንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
  7. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው የዕቃ አይነቶች ናሙና ማቅረብ እና በናሙና ለማቅረብ የሚያስቸግሩትን በፎቶ በማምጣት ጨረታው ከመዘጋቱ ቀደም ብለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ለማይቀርብባቸው የእቃ አይነቶች በሚቀርበው የእቃ መግለጫ(specification) መሰረት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ናሙናዎች በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ተመላሽ ይሆናል፡፡
  8. ጥቃቅንና አነስተኛ እቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በትምህርት ቤቱ ስም የተጻፈ ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. አሸናፊው ያሸነፈበትን እቃ የትምህርት ቤቱ የእቃ መረከቢያ እስቶር ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ ይኖርበታል።
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው(10ኛ) ቀን በአስራ አንድ ሰአት (11፡00) ታሽጎ በአስራ አንደኛው (11ኛ) ቀን በአራት ሰዓት(4፡00) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  11. አሸናፊው ውል ገብቶ እቃዎቹን ከማስገባቱ በፊት የውል ማስከረከቢያ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት ጥቃቅንና አነስተኛ እቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የማነብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወይራ ሰፈር አደባባይ ፊት ለፊት ገባ ብሎ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 369 6814/011 349 0998
የኮልፌ ቀራጓዮ ክ/ከተማ የየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት