Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የለማ እርሻ መሬት፣ የሕንፃ ግንባታዎች፣ የእርሻ መገልገያ መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቶ ተድላ አብርሃ ካበው ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበደረውን የብድር ገንዘብ ከባንኩ ጋር በገባው የብድር ውል መሠረት የተበደረውን የብድር ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ ፈቃደኛ ስላልሆነ ባንኩ ለብድሩ አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን የመያዣ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የመያዣ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የሚሸጠው ንብረት ዓይነት |
የመያዣ ንብረት ዝርዝር መረጃ |
ቀሪ የመሬት ሊዝ ውል (በዓመት ) |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር |
የሐራጅ ደረጃ |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ ቀንና ሰዓት |
1 |
ተድላ አብረሃ ካበው |
በጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መንግስት ኢታንግ ልዩ ወረዳ ዋንኬ ቀበሌ |
የለማ እርሻ መሬት |
በ500 ሄክታር መሬት ላይ የተቋቋመና 474.60 ሄክታር የለማ የእርሻ መሬት ያለው |
34
|
22,139,653.67
|
የመጀመሪያ
|
ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከ4፡00 እስከ 6፡00
|
የሕንፃ ግንባታዎች |
ሁለት የሠራተኛ የመኖሪያ፣ ቢሮ፣ ሁለት መጋዘን፣ ጋራጅ እና የጥበቃ ቤት ያለው |
|||||||
የእርሻ መገልገያ መሳሪያዎች |
አንድ DEUTZ FAHAR ትራክተር 70HP 2011 ስሪት ሁለት ባለ 24 Disck መከስከሻ አንድ ባለ 4 Disck ማረሻ አንድ መዝርያ እና አንድ የኬሚካል መርጫ |
|||||||
ተሽከርካሪ |
አንድ ጃፓን ስሪት ደብል ጋቢና ቶዮታ ፒካፕ 2014 ስሪት እና አንድ ጃፓን ስሪት ISUZU FSR የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ 2015 ስሪት |
የሐራጁ ሽያጭ መመሪያ
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% /ሃያ አምስት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (C.PO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በጨረታው እንዲሳተፍ ከድርጅቱ የተሰጠ የውከልና ሰነድ እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መከፈል ይኖርበታል።
- በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ገዢ እንዲከፍል በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ እና ያልተከፈለ የመንግስት ታክስ እና ቀረጥ ካለ ገዥ ይከፍላል።
- ለገዥው ስመ ንብረት እንዲዛዎርለት ባንኩ ለሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤ ይጽፋል።
- ሽያጩ የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው።
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለሙነብኘት የሚፈልግ ማንኛውም የሐራጅ ተሳታፊ በስልክ ቁጥር 0115-53-89-34 ወይም +251475512588 በመደወል ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
- ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚፈልግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት፣
- በስልክ ቁጥር፡_ +251475512588 ወይም +251471518284 በመደወል መጠየቅ ይችላል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት