Your cart is currently empty!
በሮቤ ከተማ የአዶሼ ወለሼ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የደንብ ልብሶች እና የስፌት ዋጋ፣ ህትመቶች፣ የፐትሮል ትዮታ መኪና፣ ጎማ እና መለዋዎጫ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሮቤ ከተማ የአዶሼ ወለሼ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ በክ/ከተማው ስር ላሉ መ/ቤቶች
- የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
- የደንብ ልብሶች እና የስፌት ዋጋ ህትመቶች፣
- የፐትሮል ትዮታ መኪና ፣ጎማ እና መለዋዎጫ እቃዎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል።
ስለዚህ በዘርፉ ፍቃድ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች እዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
- ቲን ነምበር Tin No እና VAT ወይም TOፐ ተመዝጋቢ መሆናችሁን የዘመኑን ግብር የከፈላችሁበትን ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን የውድድር ዓይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ/CPO/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ከአዶሼ ወለሼ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለጽህፈት፣ ለኤሌክትሮኒክስ፣ ለጽዳትና፤ ለቋሚና አላቂ ዕቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ብቻ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የኮምፒዩተር ጥገና ህትመት፣ የምግብ እና ሻይ ቡና አቅራቢዎች ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ብቻ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ አቅራቢዎች የውል ማስከበሪያ የዕቃውን ሙሉ ዋጋ 10% ኮንትራት አማውንት ( በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ብቻ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በቀረበው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ከ5 ቀን በኋላ በመስሪያ ቤቱ ቀርበው ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ውል ከገቡ በኋላ በ15 ቀን ዕቃውን ማስገባት አለባቸው፡፡
- የዕቃዎቹን ዋጋ መ/ቤቱ የሚከፍለው ንብረቱ ሙሉ በሙሉ ንብረት ክፍል ገቢ ሆኖ በጥያቄው መሠረት መቅረቡ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
- ዕቃዎቹ ገቢ ሆነው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ለአላቂ ዕቃዎች የ1 ወር፣ ለቋሚ ዕቃዎች የ1 ዓመት ጊዜ ጋራንት/ዋስትና/ መስጠት የሚችልና ዕቃዎቹ የተበላሹና ኦርጅናል ካልሆኑ ለመመለስ ግዴታ የሚገባ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ናሙና ማቅረብ የሚችል ሲሆን ሠነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- በተራ ቁጥር 6 የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ለማቅረብ የምትጫረቱ ተጫራቾች የዕቃ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከሠነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃውን /Brand Name/ መሙላት አለባቸው፡፡ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ተወዳዳሪዎች አገልግሎቱን የምትሰጡት ንብረቱ ባለበት ቦታ ድረስ በመገኝት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች የማጓጓዢያ፣ ማስጫኛና ማውረጃ ወጪውን በመቻል አዶሼ ወላሼ ከ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ አዶሼ ወላሼ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር፡– 09 12 26 56 34 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በሮቤ ከተማ አስተዳደር የአዶሼ
ወለሼ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Electrical, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx