Your cart is currently empty!
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወ13 ጀሞ አካባቢ የቡርቃ ዋዮ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎች ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወ13 ጀሞ አካባቢ የቡርቃ ዋዮ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚገዙ ዕቃዎች ማለትም፣
1. አላቂ የቢሮ ዕቃ (ሎት 2)
2. የደንብ ልብስ (ሎት 1)
3. የጽዳት እቃዎች (ሎት 4)
4. ሕትመት (ሎት3)
5. ቋሚ እቃዎች (ሎት6 )
6. የላብራቶሪ ዕቃዎች (ሎት5 )
7. የጥገና ዕቃዎች (ሎት7)
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፤
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አላቂ የቢሮ ዕቃ (ሎት 2) 10,800 ብር፣ የደንብ ልብስ (ሎት1) 15,000 ብር፣ የጽዳት እቃዎች (ሎት4) 12,000 ብር፣ የጥገና ዕቃዎች (ሎት5) 500ብር፣ ቋሚ እቃዎች (ሎት 6) 5000፣ የላብራቶሪ ዕቃዎች (ሎት6) 300 ብር፣ ሕትመት (ሎት3) 500 ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO)ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከተደራጁበት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ) ብር በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወ 13 አካባቢ ስፕሪንግ ኦፍ ኖውሌጅ አካዳሚ ት/ ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው የቡ/ዋ/የመ/ደት/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ፋይናንስና ግዥ ቢሮ ቁጥር 1 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ቀን በ4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ከሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት1፣ ሎት2 እና ሎት4 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት5 የፎቶ ናሙና ማቅረብ በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ያሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከ ወ3 ጀሞ 1 አካባቢ ከሸራ መስጅድ ዝቅ ብሎ ስፕሪንግ ኦፍ ኖውሌጅ ት/ቤት ፊት ለፊት የቡ/ዋ/ የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 1
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 22 18 59 54
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ወ13 የቡርቃ ዋዮ የመ/ደ/ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Electrical, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Laboratory Equipment and Chemicals cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx