Your cart is currently empty!
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የአዳጊ/ቄብ ዶሮ እና መኖ ግዥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በሌማት መርሀ–ግብር የአዳጊ/ቄብ ዶሮ እና መኖ ግዥ ጨረታ ቁጥር 04/2018ዓ/ም
ሎት-04 ግዥ ለመፈፀም የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለ2017/18 ዓ/ም በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፤ ለ2017/18 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በሀገር ውስጥ ገቢዎች የጨረታ ተሳታፊነት ተሳታፊነት የድጋፍ ደብዳቤ ያለውን፤ የታደሠ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ዝርዝር ጨረታውን የያዘ ሠነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል አሶሳ በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይቻላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ስምምነት ሲፈርም ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል፡፡
- በጨረታው ያልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበረያ የጨረታ አሸናፊ እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግባት እስከ 16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ ነገር ግን ቅዳሜ፤ እሁድ እና የህዝብ በዓል ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘጋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ በሚገኘው በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይሆናል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-057 775 2144 አሶሳ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ