Your cart is currently empty!
ሀና ቅ/አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ጥገና እና ህትመት ስራዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001
ሀና ቅ/አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ጥገና እና ህትመት ስራዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ ቢታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ሎት |
የአቃው/አገልግሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ሎት 1 |
የፅህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
20,000 |
ሎት 2 |
የደንብ ልብስ |
25,000 |
ሎት 3 |
የፅዳት እቃዎች |
27,000 |
ሎት 4 |
የትምህርት እቃዎች |
3000 |
ሎት 5 |
ቋሚ ዕቃዎች |
11,000 |
ሎት 6 |
የጥገና ዕቃዎች |
7000 |
ሎት 7 |
የህትመት ስራዎች |
2000 |
2. ተጫራቾች ከዚህ በላይ በሠንጠረዥ በተመለከተው መሰረት በሚወዳደሩበት ሎት ፊት በፊት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ሀና ቅአንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በየሎቱ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመከፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 14 ልዩ ስሙ ሰፈራ ሀና ቅአንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 003 በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል።
4. ጥቃቅን እና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች አምራች በሆኑበት ዘርፍ ላይ ብቻ ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
5. ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነቫቱ ሞልተውና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርገው ማቅረብ አለባቸው።
6. የጨረታ ሰነዱ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በዓል ካልሆነ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካያቸው ባሉበት ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጨረታ ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በግልፅ ለይቶ በመፃፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ አለበት።
8. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ሰፈራ ታክሲ ተራ ፊት ለፊት ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 011 8 29 01 64 /011 8 29 01 65
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 14 ሀና ቅ/አንደኛ አንደኛና እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት