በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የተለያዩ የሞተር ሳይክልና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

ቁጥር ጨ01/2018

በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር በ2018 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም

  • ኤሌክትሮኒክስ
  • ፈርኒቸር
  • የጽህፈት መሳሪያዎች
  • የፅዳት ዕቃዎች
  • የደንብ ልብስ
  • የተለያዩ የሞተር ሳይክልና የመኪና ጎማዎች

በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ መስፈርት/ በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን (2017/2018) ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ቫት ከፋይ የሆኑ እንዲሁም TI Number ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሂደት ከገባ በኋላ በሰነዱ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሀሳቤን ቀይሬአለው ማለት አይችልም።
  3. ማንኛውም ዕጩ ተወዳዳሪ የጨረታውን ሂደት ለመስተጓጓል ቢሞክር ከጨረታው ውጭ እንዲሆን ተደርጎ ወደፊት በሚደረገው የመንግስት ግዥ ላይ እንደይሳተፍ የሚደረግ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል።
  4. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
  5. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፈቃዳቸው ዘርፍ ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት።
  6. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የግዥ መደብ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት ነገር ግን በካሽ ከሆነ ወንዶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000205079606 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢንታዬ ቅርንጫፍ ገቢ ተደርጎ computer generated slip መቅረብ አለበት።
  7. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዕቃ ጥራት ደረጃቸው አስቸጋሪ የሆኑ የዕቃ አይነቶችን መስሪያ ቤታችን ቀድሞ ስላዘጋጀ ለምሣሌ የኮምፒውተር፣ ወረቀት፣ እስክሪብቶዎች፣ ኬንት፣ ሶፍት፣ ኡሁ አጀንዳ፣ የኮምፒውተር ቀለም ኦርጅናል፣ የቆዳ ውጤቶች ቦርሳዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪ ድርጅቶች ይህን ናሙና መሰረት በማድረግ ብቻ የምንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
  8. አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን ጭነው እስከ መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች ዕቃው የተሰራበትን የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበትን ዓ.ም መግለፅ አለባቸው
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት እንዲሁም እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት:: በራሳቸው ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችን አመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም።
  12. ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን እቃዎች እስከ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
  13. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥራቸውን በትክክል ጽፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  14. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ወይም ለሁለት ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።
  15. መ/ቤቱ ጨረታውን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ውድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ እቃው አይነት ወይም የሚፈለገው አገልግሎትን መሰረት በማድረግ ጥራትን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ውድቅ የሚያደርግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀረቡ ዕጣ ተጥሎ የሚሰጥ ይሆናል ።
  16. የሰነዱ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን ከ24/12/2017 ዓ/ም እስከ 13/01/2018 ሲሆን ጨረታው በ11፡30 ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ የሚከፈተው በ14/01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኙበት በወንዶ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በይፋ ይከፈታል።
  17.  የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከወንዶ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በወንዶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000205079606 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ቢሮ ቁጥር 01 ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ተወዳዳሪ ደርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰአት የሰነዱ ሽያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  18. የጨረታ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ስለሚሸጥ በውሉ መሰረት ጨረታውን ያሸነፈው ነጋዴ ለውሉ ተገዥ መሆን አለበት።
  19. ማንኛውም ተጫራች ከቫት ውስጥ 7.5% እና 2% (3%) ለወረዳ የሚቆርጥ ይሆናል።
  20. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  21. አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ ወንዶ ወረዳ ገንዘብ
  • ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000205079606 በኢትዮጵያ ንግድ ገቢ ማድረግ አለበት።
  • ለበለጠ መረጃ 046 1140006/0461140011 ሞባይል 09 11043416/0936459025

በምዕራብ አርሲ ዞን የወንዶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት