Your cart is currently empty!
በን/ስ/ላ/ከ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2018ዓ/ም የበጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ ለስራና ለትምህርት አገልግሎት የሚያስፈልጉትን ለካፌና መስተንግዶ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮና ህትመት እቃዎች፣ አላቂ የት/ት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የአይሲቲ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
በን/ስ/ላ/ከ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2018ዓ/ም የበጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ ለስራና ለትምህርት አገልግሎት የሚያስፈልጉትን ለካፌና መስተንግዶ፣የጽዳት ዕቃዎች፣አላቂ የቢሮና ህትመት እቃዎች፣ አላቂ የት/ት እቃዎች፣ቋሚ እቃዎች፣የደንብ ልብሶች እና የአይሲቲ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤የዘመኑ ግብር የከፈለ፤ በመ/ግ/ን/አስ/የእቃ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ* ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 150.00 (አንድመቶ ሃምሳ ብር) ብቻ ረዳት ፋይናንስ ቢሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስተና በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (0.5%-2%) በእያንዳንዱ ሎት በተበጀተለት በጀት መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለካፌና መስተንግዶ ሎት 001-5,140.00
- ለጽዳት እቃዎች ሎት 002-5,824.00
- ለአላቂ የቢሮና ህትመት እቃዎች ሎት 003-15,790.00
- ለአላቂ የት/ት እቃዎች ሎት 004-9,424.00
- ለቋሚ የቢሮ እቃዎች ሎት 005-25,384.00
- ለደንብ ልብስ ሎት 006-33,719.00
- ለአይሲቲ ጥገና ሎት 007-8,489.00
4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የጥራት ደረጃና ለአስተማማኝነቱ ለእያንዳንዱ እቃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል። በ11ኛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል።
6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት በተመረጡ ናሙና መሰረት እቃዎችን ትምህርት ቤት ድረስ ማምጣት እና ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ወረዳ 06 ጎፋ ገብርኤል ዝቅ ብሎወደ ጎፋ ካምፕ በሚወስደው መንገድ (ከመስቀል ከትፎ በስተጀርባ ገባ ብሎ ቀበሌ 52 ፊትለፊት)
ለበለጠ መረጃ 011-4-66-18-78
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት