በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ /ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር /ቤቶች 2018 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች

  • 1. የተለያዩ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
  • 2. ፈርኒቸሮች
  • 3. ኤሌክትሮኒክስ
  • 4. የጽህፈት መሳሪያዎች
  • 5. የጽዳት መሳሪያዎች
  • 6. ሞተር ሳይክሎች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በዘርፉ የስራ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ካሟሉ መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

2. ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15(አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 600 (ስድስን መቶ ብር) በመክፈል በቀርጫ ከተማ ገንዘብ /ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦሪጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦሪጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡

6. ጨረታው 26/12/2017 . እስከ 5/1/2018 . 500 ሰዓት ተዘግቶ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በቀርጫ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ይከፈታል፡፡

7. አሸናፊው አካል እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡

8. አሸናፊው በጨረታ መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10/ቀን ውስጥ ለጨረታ ውል ማስከበሪያ የሚውል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ቼክ(CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ይህ ባይፈጸም ቀደም ሲል ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

9. ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ /ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣትና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በራሱ ወጪ ማንጣጠም የሚችል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ:- ሞባይል ቁጥር 0936 4001 83/0911 104 708

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ /ቤት