Your cart is currently empty!
በየካ ክ/ከ የወ 01 ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ1ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የደንብ ልብሶች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመቶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የጥገና እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች እና የኮምፒውተሮች እና ኮፒማሽኖች ፕሪንተሮች ጥገና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከ የወ 01 ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ1ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን የደንብ ልብሶች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች ህትመቶች የጽዳት እቃዎች የጥገና እቃዎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቋሚ እቃዎች እና የኮምፒውተሮች እና ኮፒማሽኖች ፕሪንተሮች ጥገና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1፡– የደንብ /የስራ ልብስ
- ሎት-2 ፡– የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት3 ፡–ህትመቶች
- ሎት -4፡–የጽዳት እቃዎች
- ሎት-5 የጥገና እቃዎች
- ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 7፡–ቋሚ እቃዎች
- ሎት 8/የኮምፒውተሮች እና ኮፒማሽኖች ፕሪንተሮች ጥገና
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች
1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ከፋ/ኢ/ል/ ሚኒስቴር በእቃ ግዥ አቅራቢነት ለተወዳዳሪነት የተፈቀደበት የምዝገባ ማስረጃቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር /ብቻ በየሎቱ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ከተቋሙ ግዥ ከፍል መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ከነቫት በመሙላት እና ስም፤ ፊርማና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በተቋሙ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብር 7000.00 /ሰባት ሽህ ብር ብቻ በማሰራት ዋናውን/ኦርጅናል ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በይፋ ይከፈታል።
6. እቃዎቹ በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት መቅረብ አለባቸው ኤክስፓየርድ ዴት ለሚያስፈልጋቸው የተመረቱባቸውና ኤክስፓየርድ ጊዜያቸው በግልጽ የሚታይ መሆን አለባቸው የአገልግሎት ጊዜያቸው ቢያንስ አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው።
7. ዋጋችሁን ስትሞሉ የምትሞሉትን ዋጋ ጠቅላላ ድምር እንድታስቀምጡ፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡– ፈረንሳይ ወደ አርባ አንድ እየሱስ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ከወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ፡፡
ለበለጠ መረጃ : ስ.ቁ 011 154 9680
የካ ክ/ከ የፈረንሳይ አካባቢ ጤና ጣቢያ