Your cart is currently empty!
የዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር በወረዳው ለሚገኙ ለገጠር ቀበሌዎችና ሴክተር መስሪያ ቤቶች የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን (ፈርኒቸር)፣ አላቂ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር በወረዳው ለሚገኙ ለገጠር ቀበሌዎችና ሴክተር መስሪያ ቤቶች የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን (ፈርኒቸር)፣ አላቂ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጸውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
5. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልቶ ካልቀረበ እና ማንኛውም ስህተት ቢፈፀም ኃላፊነቱ የተጫራቹ/የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል።
6. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልጽ መፃፍ ይኖርበታል፤ እንዲሁም የዱግዳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ መሙላት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ (lot) 5000 (አምስት ሺህ) በCPO ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ያቀረበው ዋጋ ለሶስት (3) ወር ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የዋጋ ለውጥ የሚካሄደው ከሶስት ወር በኋላ በገበያ ጥናት ውስጥ እና አሸናፊ ድርጅት በሚያቀርበው ዋጋ ተንተርሶ በሚሰጥ ዋጋ ይሆናል።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ኦሪጅናል (original) መሆን ይኖርባቸዋል።
10. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል።
11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
12, የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) የስራ ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
13. አሸናፊው ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ለጠቅላላ ዋጋ 10/100 ለመስሪያ ቤቱ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
14. ማንኛውም ተጫራች መስሪያ ቤቱ በሰጠው የናሙና ዝርዝር ዕቃዎች መሰረት በአካል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅበታል።
15. ከዚህ በላይ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2001 እና 1/2009 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 157/2002 መሰረት ጽ/ቤቱ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0913 851 391 / 0932 319 192 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡– በምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳደር የዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
መቂ
በምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳደር የዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት