የጨፌ ከራቡ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችንና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የዕቃ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 01/2018

የጨፌ ከራቡ ገንዘብ /ቤት 2018 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት /ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡

የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችንና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የመወዳደሪያ መስፈርት

1. በንግድ (በስራ) ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የስራ ፍቃድ ያላቸውና በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

2. እቃ አቅራቢዎች በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ለመመዝገባቸው የታደሰ ሕጋዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ብር 10.000 /አስር ሺህ/ ማስያዝ የሚችሉ፣

4. እቃ አቅራቢው የሚገዛውን እቃ በራሱ የማጓጓዣ ወጪ መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችል፣

5. የሚቀርበው ቋሚ የቢሮ ዕቃ ያልተገጣጠሙ ከሆኑ በራሱ ወጪ ማስገጠም የሚችል፣

6. የሚወዳደሩባቸውን የዕቃ አይነት ማለትም ለአላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ አላቂ የጽዳት እቃዎችና ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ

1. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርባቸው የምስክር ወረቀቶች በጉልህ የሚታዩና የሚነበቡ መሆን አለባቸው፡፡ የቀረበው ማስረጃ ግልጽነት የሌለውና የማይነበብ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም፡፡

2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት በመወዳደሪያ ሓሳብ ሰነድና የጨረታውን መመሪያ ስለመቀበላቸው የሚያረጋግጥ በጨረታ ሰነዱና የጨረታ መመሪያ ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው ስልጣን ባለው አካል በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በመለየት በፖስታ (Envelope) በማድረግና በሰም በማሸግ በአንድ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ማቅረብና አስመዝግቦ በጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡ በቀረበው የጨረታ መመሪያና የጨረታ ሰነዶች ላይ ካልተፈረመና የድርጅቱ ማህተም ካልተደረገበት የጨረታ ሰነድ አካል የሆነውን የተጫራቾች መመሪያ እንዳልተቀበሉ በመቁጠር ያቀረቡት የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ውጪ ወይም ውድቅ ይሆናል፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታው መሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ጊዜ ጀምሮ ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ግን ውል ከተፈራረሙና የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ካስያዙ በኋላ ተመላሽ ይሆናል

4. ማንኛውም ተጫራች የተጠቀሰውን መስፈርት ያላሟላ ሰነድና ከላይ የተቀመጠውን እቃ ሳምፕል (ናሙና) ያላቀረበ እንደሆነ ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡

5. አንድ ተጫራች ሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡

6.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጨፌ ካራቡ ገንዘብ /ቤት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ክፍል የቢሮ ቁጥር 05 በአካል በመቅረብ የአንድ ጥቅል (Lot) የጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

7. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቅያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4:15 ጨፌ ከራቡ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ክፍል የቢሮ ቁጥር 05 ጨረታው ይከፈታል፡፡

8. 16ኛው ቀን ከሥራ ቀን ውጪ ቅዳሜ ወይም እሑድ ቀን ላይ የሚውል ከሆነ ሰኞ ዕለት የሚከፈት ይሆናል፡፡

9. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ በሸገር ከተማ አሰተደደር የፉሪ ክፍለ ከተማ የጨፌ ከራቡ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ያገኙናል።

ለበለጠ መረጃ : የስልክ ቁጥር 09 11 72 95 89, 09 25 40 69 31

በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ / የጨፌ ከራቡ ወረዳ ገንዘብ /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *