የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአራዳ /ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት 2018 . በጀት አመት የአንደኛ (1) ዙር ጨረታ፡በሎት1፡የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በሎት2የደንብ ልብስ ግዥ በሎት 1አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በሎት4የደንብ ልብስ ግዥ በሎት5የመኪና ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አውዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ በተጨማሪም በአገልግሎት ስራዎች በሎት 1የመስተንግዶ ስራዎች በሎት 2የህትመት ስራዎች በሎት 3የኤሌክትሮኒክስ (የአይቲ) እቃዎች ጥገና ስራዎች በሎት4የኤሌክትሮኒክስ (የአይቲ) እቃዎች መለዋወጫ አቅርቦት በሎት 5የልብስ ስፌት ስራዎች በሎት 6የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ጥገና ስራዎች በሎት 7የዲኮር ስራዎችን በሎት 8 የትራንስፖርት አገልግሎት ስራዎች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

1. ተጫራቾች በአቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. የታደሰ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡

4. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ፡፡

5. የጨረታ ሰነዱ የመወዳደሪያ ዋጋ በሙሉ ታሽጎ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት ሁሉ ናሙና ማቅርብ አለባቸው ::

7. ተጫራቾች በአንድ እቃ አይነት ሁለት ናሙና ማቅረብ የለባቸውም::

8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት ሁሉ ናሙና ላይ ድርጅታቸውን የሚገልፅ ማንኛውንም ምልክት (ማህተም) ማስቀመጥ የለባቸውም::

9.ተጫራቾች የጨረታው ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር በየሎቱ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረዳ 5 ፋይናንስ /ቤት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

10. ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን 400 ሰዓት የሚታሸግ ሲሆን 430 ሳጥኑ የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. የመወዳደሪያ ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይሆናል፡፡

12. ተጫራቾች ዋጋቸውን በወሰዱት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

13.ተጫራቾች በወሰዱት ሰነድ ላይ በእስክሪቢቶ እስፔክ ማስተካከል አይችሉም፡፡

14. የጨረታ ዋስትና በየሎቱ 2% ሲፒኦ ብቻ ሲሆን የምንቀበለው ቼክ አንቀበልም በተጨማሪም ተጫራቾች አሸናፊ ሆነው ሲቀርቡ አሸናፊ የሆኑበትን 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

15. ተጫራቾች የዋጋ የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ አይችሉም::

16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ለማግኘት ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር

01111 266 384በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ ፒያሳ ገዳም ሰፈር ከጊዮርጊስ ጀርባ ወደ ዳክስን መሄጃ ወረዳ 5 ፋይናንስ /ቤት 2 ፎቅ።

የአራዳ /ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር

ፋይናንስ /ቤት