Your cart is currently empty!
ለሚ አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት |
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ |
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
8,000.00 |
ሎት 2 |
አላቂ የቢሮ እቃ |
7,000.00 |
ሎት 3 |
ህትመት |
2,000.00 |
ሎት 4 |
የህክምና ዕቃዎች |
3,000.00 |
ሎት 5 |
አላቂ የትምህርት ዕቃዎች |
5,000.00 |
ሎት 6 |
የፅዳት ዕቃ |
8,000.00 |
ሎት 7 |
ልዩ ልዩ መሣሪያ ግዥ |
2,000.00 |
ሎት 8 |
የሕንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ መግዣ |
5,000.00 |
ሎት 9 |
ጥገና እድሳት |
3,000.00 |
ሎት 10 |
ኤሌክትሮኒክ |
10,000.00 |
ሎት 11 |
ፈርኒቸር |
9,000.00 |
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበውመወዳደር ይችላሉ፡፡
- ሕጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር (TIN No.) ሊኖራቸውና ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሚያቀርቡት ዕቃ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ እና የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለእያንዳንዳቸው የዋጋ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (C.PO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በለሚ አፀደ ሕፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ መግዛትና መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በመለየትና በ2 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በለሚ አፀደ ሕፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ቢሮ ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በቀኑ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ከሚገዛው አጠቃላይ ዕቃዎች 20% መጨመር እና መቀነስ ይችላል ፡፡
- ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሁሉም ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ሲያቀርቡ ምንም አይነት የድርጅቱን ማንነት የሚገልጽ ምልክት መኖር የለበትም።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 667 -7635 ወይም በአካል ለሚ አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር ገባ ብሎ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ትንሽ ወረድ ብሎ ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ ሂደት በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት