Your cart is currently empty!
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኝ ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት እቃዎች፣ እስቴሽነሪ እቃዎች፣ የቋሚ የፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የህትመት ስራ፣ መድሃኒትና የህክምና እቃዎች እና የፓረቲሽን ስራ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Lessan(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኝ ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ሎት 1 የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 4000 ብር
- ሎት 2 የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 4000 ብር
- ሎት 3 እስቴሽነሪ እቃዎች የጨረታ ማስከበርያ 4000 ብር
- ሎት 4 የቋሚ የፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የጨረታ ማስከበርያ 7000 ብር
- ሎት 5 የህትመት ስራ የጨረታ ማስከበርያ 5000 ብር
- ሎት 6 መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች ጨረታ ማስከበርያ 7000 ብር
- ሎት 7 የፓረቲሽን ስራ ጨረታ ማስከበርያ 7000 ብር
ስለዚህ ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፋላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት የግ/ን/አስ/ ኤጀንሲ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ቢቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ጨረታውን በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ጋር ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እዲሁም የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖረባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቶች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣ ሎት 2፣ ሎት 3 የዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ሎት 4 ድርጅቱ የሚያቀርበዉን እቃ በፎቶ እና ማኑዋለ ዝርዝሩን በእስፔኩ መሰረት በፖስታ አሽጎ በሳምፕል መልክ ለግዢ ክፍል ማቅረብ አለበት እዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ የመስሪያ ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ድርጅታቹ ባለበት ቦታ ሄዶ እቃውን የሚያይ ይሆናል፡፡ በሎት 5 ደሞ መስሪያ ቤቱ ሳፕል በሚሰጠው መሰረት ዋጋ የሚሞላ ይሆናል በሎት 6 ተጫራች ባስገባው ዋጋ የሚወዳደር ሲሆን በሎት 7 ደግሞ ተጫራች መስሪያ ቤቱ ባስቀመጠው ዲዛይን እና ቦታውን በአካል አይቶ ዋጋ የሚሞላ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል። አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ካቀረባቸው እቃዎች ውስጥ እስከ 20% ድረስ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ከቫት ጋር ተሰርቶ መቅርብ አለበት
አድራሻ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ ከአባጅፋር መስጊድ ከፍ ብሎ መሰረተ ዕድገት ት/ቤት ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር፡- 011-2-79-13-59/ 011-2-79-14-80/
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx House and Building cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Pharmaceutical Products cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx