Your cart is currently empty!
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ፅ/ቤት ስር ላሉት ፅ/ቤቶች በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Lessan(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ፅ/ቤት ስር ላሉት ፅ/ቤቶች በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን
- ሎት 1- የደንብ ልብስ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20000 ብር
- ሎት 2- የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20000 ብር
- ሎት 3- የፅዳት እቃዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20000ብር
- ሎት 4- ልዩ ልዩ እቃዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 10000 ብር
- ሎት 5- ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ CPO 10000 ብር
- ሎት 6- የመኪና ጎማ እና የተለያዩ እቃዎች ማስከበርያ CPO 30000
- ሎት 7- የቋሚ እቃ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20000
- ሎት 8- የዲኮር ስራዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 10000
- ሎት 9- የትራንስፖርት አገልግሎት የጨረታ ማስከበርያ CPO 5000
- ሎት 10- የኤሎክትሮኒክስ እና የፈርንቸር ቆሚ እቃ ጥገና ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 10000
- ሎት 11- የኤሌክትሪክ ጥገና የጨረታ ማስከበርያ CPO 5000 ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ፅ/ ቤት ስም ከላይ በተጠቀሰው አግባብ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት(ቀን) አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 1 4ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ለወረዳው ፅ/ቤት 4ኛ ፎቅ ግ/የ/ሂደት ክፍል ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን በ10፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11 ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት በወረዳው 4ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበዓል/ የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 3፣ ለሎት 4፤ ናሙና ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ሎት 7 በፎቶ እንዲሁም በስፔስፊኬሽን ማቅረብ ይጠበቅባቸል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎችና አገልግሎት፤ ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ከሆኑ መጫረት የሚቸሉት በተደራጁበት ምርት ውጤት ብቻ ሲሆን እንዲሁም ከአደራጃቸው አካል የሚጫረቱበትን እቃ ማቅረብ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ፋ/ፅ/ቤት ስልክ ቁጥር 011 554 7832
አድራሻ፡- ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር መስከረም 1 ት/ቤት ፊት ለፊት ፣
ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ፋ/ፅ/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Event Organizing and Planning cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx Hospitality, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Rent cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, cttx Warehousing, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Tour and Travel cttx, Transit and Transport Service cttx