በልደታ ክ/ከተማ ት/ት/ጽ/ቤት ካራማራ የመጀ/ደረጃ፣ ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ እና ቀበሌ 37 ቅ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ ክ/ከተማ ት/ት/ጽ/ቤት ካራማራ የመጀ/ደረጃ፣ ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ እና ቀበሌ 37 ቅ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሎት በዝርዝር የተገለፁትን ዕቃዎች፣

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 4 አላቂና ቋሚ የት/ት መርጃ ዕቃዎች፣
  • ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • ሎት 6 የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸር መገልገያ ዕቃዎች፣
  • ሎት 7 የተለያዩ የህትመት ስራዎች
  • ሎት 8. የመስተንግዶ ውሃ እና ቆሎ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት

2. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ

3. በአቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት

4. የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን እንዲሁም በዋጋ መሙያው ላይ ሳፕል እንዲቀር ብባቸው የተገለፁትን ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን በሎት 6 የተገለፀውን ዕቃ በማምረቻ ወይም በመሸጫ ቦታችሁ ማሳየት ያለባችው ሲሆን ለጨረታው ማስከበርያ የሚሆን ለሎት 1 12000.00 /አስራ ሁለት ሺ ብር/፣ ሎት 2. 10000.00 /አስር ሺ ብር/፣ ሎት 3. 10000.00 /፣ አስር ሺ ብር/፣ ሎት 4. 10000.00 /አስር ሺ ብር/፣ ሎት 5. 15000.00 /አስራ አምስት ሺ ብር/ ሎት 6. 10000.00/አስር ሺ ብር/፣ ሎት 7. 3000.00/ ሶስት ሺብር/፣ ሎት 8. 2000.00/ ሁለት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በሁለት ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ት/ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ት/ቤቱ ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ዋጋችሁን በመሙላት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰነዳችሁን በማስገባት መወዳዳር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የጨረታ ሰነድ በደብዳቤ የምናስተናግደው አምርታችሁ ለገበያ በምታቀርቡት ምርት ላይ ብቻ ነው።

ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት /አስራ አንድ ሰዓት/ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ሲከፈት የማይገኙ ተጫራቾች ጨረታው በሌሉበት እንደሚከፈት እያሳወቅን የመክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

  • ማሳሰቢያ፡- ት/ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  • ማሳሰቢያ፡- የምታቀርቡት ናሙና (ሳምፕል) ላይ የድርጅታችሁን አርማ ማሃተም ማድረገረግ አይቻልም!!
  • አድራሻ፡- በልደታ ክ/ከ/ወ/03 ካራማራ የመጀ/ደ/ት/ቤት አብነት አደባባይ ጆስሀንስን አጠገብ ስልክ ቁጥር 0112-73-23-45

በአ/አ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክ/ከተማ ት/ት/ጽ/ቤት ስር ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ እና የቀበሌ 37 ቅ/ አንደኛ እና የካራማራ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ጽ/ቤት