Your cart is currently empty!
በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅህፈት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የኢንተርኔት መለዋወጫዎች፣ ህትመት እና የላብራቶሪ፣ ሪኤጀንት እና የህክምና መገልገያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Lessan(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 001/2018
በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት፡–
- ሎት 1 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2. አላቂ የፅህፈት እቃዎች፣
- ሎት 3 አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 4. ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የኢንተርኔት መለዋወጫዎች,
- ሎት6 ህትመት
- ሎት 7. የላብራቶሪ፣ ሪኤጀንት እና የህክምና መገልገያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
3. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣
4. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቁባቸው እቃዎች ናሙናውን ቀድመው ጨረታ ሰነዱ ሣጥን ውስጥ ከማስገባታቸው በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
6. የህክምና መሳሪያዎች (እቃዎች ) ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት / ስትመጡ የህከምና መሳሪያዎች አቅራቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ENDA ይዘዉ መቀረብ አለባቸው
7. የህክምና እቃዎች ላይ ፋይናሽያል ለብቻ ካታሎግ እና ቴከኒካል ዶክመንት ለብቻ አጠቃላይ በ 3 ፖስታ ኮፒ ፋይናሽያል አርግናል እና ቴክኒካል በማለት ማስገባት አለባቸው።
8. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ |
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ ግዥ |
የኢትዮ ብር 10,000 |
ሎት 2 |
አላቂ የፅህፈት እቃዎች |
የኢትዮ ብር 10,000 |
ሎት 3 |
የፅዳት እቃዎች |
የኢትዮ ብር 10,000 |
ሎት 4 |
ቋሚ እቃዎች |
የኢትዮ ብር 20,000 |
ሎት 5 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች አላቂ የቢሮ እቃዎች |
የኢትዮ ብር 6,000 |
ሎት 6 |
ህትመት |
የኢትዮ ብር 8,000 |
ሎት 7 |
የላብራቶሪ፣ ሪኤጀንትና የህከምና መገልገያ እቃዎች |
የኢትዮ ብር 30,000 |
9. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 404 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።
10. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:
11. ጨረታው በ10ኛው ቀን 10፡30 ሠዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
12. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10 % ማስያዝ አለባቸው፡፡
13. ተጫራቾች ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ቋሚ ዕቃዎች (የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች) መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ለማቅረብ በቅድሚያ የራሳቸው ንግድ ፍቃድ፤ መስሪያና መሻጫ ቦታዉ ድረስ በሚመጡ ባለሙያዎች በማረጋገጥ ይሆናል፡፡ ስፔስፊኬሽን ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ፊርማ መኖር አለበት፡፡
14. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
15. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
17. ተጫራቾች በሰነዳቸው ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን በትከክል መሙላትና በማህተም መረጋገጥ አለበት፡፡
አድራሻ
ስልክ 09-86-38-96-18/ 011 888 0128
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ከማርያም ማዞሪያ 100 ሜ ገባ ብሎ