Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የመረጃ ቴከኖሎጂ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመፀዳጃ ቤት ጥገና ዕቃዎች እና የሞተር ሳይክል ጎማ እና የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት
- የደንብ ልብስ፣
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የህትመት ውጤቶች፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የመረጃ ቴከኖሎጂ ዕቃዎች
- የፅዳት ዕቃዎች፤
- የመፀዳጃ ቤት ጥገና ዕቃዎች እና
- የሞተር ሳይክል ጎማ እና የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች ግዥ
ለመፈፀም ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ፐ ሰርተፊኬት ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና መረጃ ያላቸው፤
- ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት ከሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ የደንብ ልብስ ብር 7,600 (ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ብር)፤ ለሎት ሁለት አላቂ የጽሕፈት ዕቃዎች 17,000 (አስራ ሰባት ሺህ ብር)፣ ለሎት ሦስት የህትመት ውጤቶች ብር 9,000 (ዘጠኝ ሺህ ብር)፣ ለሎት አራት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች እና የቢሮ መስኮት መጋረጃ ብር 18,000 (አስራ ስምንት ሺህ ብር)፣ ለሎት አምስት የመረጃ ቴከኖሎጂ ዕቃዎች 4000 (አራት ሺህ ብር) ብቻ፣ ሎት ስድስት የፅዳት ዕቃዎች ብር 2600 (ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ብር)፤ ሎት ሰባት የመፀዳጃ ቤት የጥገና ዕቃዎች 5000 (አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት ስምንት የሞተር ሳይከል ጎማ እና የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች 7000 (ሰባት ሺህ ብር) ሲፒአ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በቅሎ ቤት (ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት) ዳቢ ቤኛ ታወር 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚመረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለብቻ በማድረግ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ማዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- 8. የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፡፡
- 9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0114-70 52 41/011470-58-17
አድራሻ፡ ብቅሎ ቤት ግሎባል ሆቴለ ፊት ለፌት ዳቤ ቤኛ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር
ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Sanitary and Ceramics cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, cttx Tri Wheeler, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Motorcycles and Bicycles Purchase cttx