አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት እና ቋሚ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል


Addis Lessan(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/ 616/2017

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቋሚና የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት በ2018 በጀት አመት ለወረዳዉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት መስፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት

  • ሎት-1. የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት
  • ሎት-2. ቋሚ ዕቃ

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይፈልጋል።

1. ከላይ በተራ ቁጥር ከ1—2 ለተጠቀሱት እቃዎች አግባብነት ያለው ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ወረቀት ኮፒ በገቢዎች የጨረታ መሳተፊያ ጊዜን የሚገልፅ ደብዳቤ ያለው በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም 100000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ ዕቃ /አገልግሎት/ የሚያቀርቡ ድርጅቶች የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት አስኮ ኖክ ማደያ አለፍ ብሎ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ በመገኘት ለእያንዳንዱ ሰነድ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (1%)ቱን ያለውን የእቃውን ዋጋ ወደ ብር ተቀይሮ እያንዳንዱ ዋጋ በሎት1 1% 5000 ለሎት2 1% 5000 በባንክ በተረጋገጠ (Cpo) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ በማድረግ ጨረታው በአየር ላይ እስከዋለበት የመጨረሻ ቀን ድረስ እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የእያንዳንዱ እቃ የሚሸጡበት ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻውን ስማቸዉንና የጨረታ አይነት በመጥቀስ የድርጅቱን ማህተም በመሳረፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የተጠቀሱት እቃዎች ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ።

6. የጨረታው ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።

7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 2፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ 1ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት።

9. ወረዳው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች ለክፍያ ስትመጡ ደረሰኛችሁ ብርሃንና ሰላም የታተመ መሆን እንዳለበት አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጂት እንድተደርጉ

11. ተጫራቾች የገዙት የድረጅቱ ሙሉ ሰነድ ሁሉም ገፅ ላይ የተቋሙን ማህተም በማድረግ ጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።

አድራሻ ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት አስኮ ኖክ ማድያ አለፍ ብሎ ስልክ ቁጥር 09-84- 659144

ማሳሰቢያ፡– እያንዳንዱ ሰነድ በየሎቱ በተለያዩ ፖስታ ተሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ እንዲሁም ጨረታው ከመታሸጉ በፊት የጨረታ ሰነዱንና ሳንፕሎችን መቅረብ አለባቸው፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ በሚያመርቱት ምርት እና ካደራጃቸው አካል በሚቀርበው ህጋዊ ድጋፍ በንግድ ዘርፉ በተሰማሩበት (በሚቀርበው ድጋፍ ደብዳቤ መሠረት) ይስተናገዳሉ።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *