Your cart is currently empty!
የከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የትምህርት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች) የህትመት፣ የህክምና ዕቃዎችና መሳሪያዎች እና የተለያዩ ጥገናዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Lessan(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም
የከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት መስፈርቱን የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላለቹ።
- ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት 2 የደንብ ልብስ
- ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 4 ቋሚ እቃዎች(ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርንቸሮች
- ሎት 5 የህትመት
- ሎት 6 የህክምና ዕቃዎችና መሳሪያዎች
- ሎት 7 የተለያዩ ጥገናዎች
ተወዳዳሪዎች በዘርፋ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት /ቫት/ ያላቸው የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በየሎት የተቀመጡትን የብር መጠን በምትወዳደሩበት ሎት በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከጨረታው ሰነዶቻቸው አይያዘ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ሎት 1 ብር 3000.00
- ሎት 2 ብር 3000.00
- ሎት 3 ብር 4000.00
- ሎት 4 ብር 3000.00
- ሎት 5 ብር 2000.00
- ሎት 6 ብር 2000.00
- ሎት 7 ብር 2000.00
በልደታ ክ/ከተማ በወረዳ 06 ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጀ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር አምስት/05 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቶች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸግ ፓስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ለጨረታ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችዉ በተገኙበት በ10ኛ ቀን 11፡30 ታሸጎ በ11ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል።
4. የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
5. ተጫራቶች የሚወደዳሩባቸው እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቶች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎቶች ለሁሉም ናሙና የሚቀርብ ሲሆን ሎት 7 በቀረበው ፍላጉት መሠረት የሚጠገነውን አይቶ ዋጋ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
7. የዘገዩ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ የጨረታ ማቅረቢያ ዋጋ ሲሞላ ሠርዝ ድልዝ ተቀባይነት የለውም።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጽመው መሰሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9. ጥቃቅን አነሰተኛ ተቋማት ከሆኑ የንግድ ፍቃዳችውን እና ግብር ስለመክፈላቸው፤ የታደሰ መሆኑን የሚገልፅ ካደራጃቸው አካል ማቅረብና የሀገር ውስጥ የምርት ውጤቶች አምራች መሆናቸው ተጠቅሶ የጨረታና የውል ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. የሠነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የጨረታ ዋጋ ፅንቶ የሚቁይበት 60/ስልሳ ቀናት ውል ከተፈረመ ቦኃላ ይሆናል፡፡ ት/ቤቱ ባጀት በጀቱን አይተዉ 20% የመቀነስ እና የመጨመር መብት አለው
አድራሻ፡- ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ድል ገቢያ አጠገብ ወይም ብስራታ ገብሬኤል አከባቢ ነዉ
ስልክ ቁጥር፡0113712933/0113201212
የአ/አ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክ/ከተማ ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት