የኮ/ቀ/ክ/ከ/የወረዳ 09 ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ
የኮ/ቀ/ክ/ከ/የወረዳ 09 ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉት

  • ሎት1. የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 4000 (አራት ሺ ብር ) 
  • ሎት2. የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ CPO 5500 ብር (አምስት ሺ አምስት መቶ ብር)
  • ሎት3 የተለያዩ የደንብ ልብስ ጨርቅ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 5000 (አምስት ሺ ብር)
  • ሎት4 . የተለያዩ የቋሚ እቃዎች ማስከበሪያ CPO ብር 27000(ሃያ ሰባት ሺ ብር)
  • ሎት5. የህትመት ውጤቶች የጨረታ ማስከበሪያ CPO 5800 ብር (አምስት ሺ ስምንት መቶ ብር)
  • ሎት6. የተለያዩ የደንብ ልብሶች ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ CPO 3000 ብር ( ሶስት ሺ ብር)
  •  ሎት7. የተለያዩ ጥገና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ CPO 10000 ብር (አስር ሺ ብር)
  • ሎት8. የተለያዩ የፕላንትና ማሽነሪ ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ CPO (1000) አንድ ሺ ብር 
  • ሎት9. ለተለያዩ የጥገና ስራዎች የጨረታ ማስከበሪያ CPO (አስር ሺ ብር)
  • ሎት 10. የመኪና ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 10000 ብር (አስር ሺ ብር )
  • ሎት 11. የተለያዩ የህክምና መገልገያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 10000 ብር (አስር ሺ ብር ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው

2. የዘመኑ ግብር የከፈለ

3. በተለያዩ ጥፋቶች ያልታገደ

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሆነ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ።

ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 አስር ተከታታይ የስራ ቀናቶች መሆኑን እየገለፅን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት ሰነዱን በመግዛት ሞልታችሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል ፡፡ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰኣት ጨረታውን ህጋዊ ተጨራቾች ተገኙም አልተገኙም ጨረታው ይከፈታል።

መስ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ — ሞቢል ምንአየ ህንፃ ፊት ለፊት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን አጠገብ

ስልክ ቁጥር 011 384 6010 ኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 09 ጤና ጣቢያ

ማሳሰቢያ-1 ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ሲመልሱ የፅህፈት መሳሪያ ለብቻው በአንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ የፅዳት እቃዎች ለብቻው አንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ ፤የደንብ ልብስ ጨርቆች ለብቻው በአንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ ፤የህትመት ውጤቶች ለብቻው በአንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ ፤የቋሚ እቃዎች ለብቻው አንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ ፤የደንብ ልብስ ስፌት ለብቻው በአንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ ፤የህክምና መገልጊያዎች ለብቻው አንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ ፤ የፕላንትና ማሽነሪ ጥገና ለብቻው አንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ ፤የጥገና እቃዎች ለብቻው አንድ ኦርጂናልና በአንድ ኮፒ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል በተጨማሪም ሳምፕሎች የፅህፈት መሳሪያ የፅዳት ዕቃዎች፤የጥገና ዕቃዎች እንዲሁም የደንብ ልብስ ሳምፕሎች ለየብቻው በኩርቱ በፌስታል መቅረብ አለበት ይህን ያላደረግ ተወዳዳሪ ከጨረታው ውድቅ የሚሆን መሆኑን እንገልጻለን።

የኮ/ቀ/ክ/ከ/የወረዳ 09 ጤና ጣቢያ