ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ወንበሮች፤ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ስካነር፣ ላብቶፕ፣ የሰዓት መቆጣጠሪያ መሳሪያ ወዘተ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብሎችንና የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን፤ የቧንቧ ዕቃዎች፤ የፋብሪካ ዎርክ ሾፕ ዕቃዎች (የተለያዩ ኩሽኔቶች፤ የዕቃ ማንሻ ቤልቶች፤ ወዘተ…..) የህንጻ ስራ መሳሪያዎች እና መገልገያ ዕቃዎች፤ እና ሌሎችም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Reporter(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

 ጨረታ ቁጥር 04/2018

ፀሐይ  ኢንዱስትሪ  አ.ማ  ቃሊቲ   ብረታ  ብረት  ፋብሪካ  ቀጥሎ የተመለከቱትን  የተለያዩ  ዕቃዎችን  በግልጽ   ጨረታ   አወዳድሮ  ለመግዛት  ይፈልጋል፡፡

  1. በሎት 1  የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ወንበሮች፤ ኮምፒውተሮች   ፕሪንተሮች ፡ ስካነር ፡ ላብቶፕ ፡ የሰዓት መቆጣጠሪያ መሳሪያ ወዘተ
  2. በሎት 2  የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብሎችንና የኤሌክትረክ ዕቃዎችን፤ የቧንቧ ዕቃዎች ፤ የፋብሪካ  ዎርክ ሾፕ  ዕቃዎች (የተለያዩ  ኩሽኔቶች ፤ የዕቃ  ማንሻ  ቤልቶች ፤ ወዘተ….. )  የህንጻ ስራ መሳሪያዎች እና  መገልገያ  ዕቃዎች፤   እና ሌሎችም፤

ስለሆነም ፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ  ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ  የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የታደሠ የንግድ  ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ማስረጃ  በሚመለከተው መ/ቤት የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ወይም በመንግስት የአቅራቢነት ዝርዝር ኤሌክትሮኒክ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ፡
  3. ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ  አካባቢ ከካፍደም ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 700 ሜትር  ገባ ብሎ በሚገኘው ከድርጅቱ የግዢ ዋና ክፍል ለየሎቱ  የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
  4. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያለው ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በጨረታው የሚወዳደሩበት የፋይናንሺያል ሠነዶቻችውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ መስከረም 06 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በፊት ዘወትር በስራ ሰዓት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000(ሃያ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው  ጋር  ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  6. ጨረታው መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ/ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 4 34 03 87

 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ፀሐይ ኢንዱስትሪ  አ.ማ