በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ የህክምና እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ህትመት፣ የተለያዩ ጥገናዎች፣ የደንብ ልብስ ጨርቅና የደንብ ልብስ ስፌት፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ፣ ልዩልዩ መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች መሳሪያዎች እና የሚወገዱ ንብረቶች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 01, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የተለያዩ ግዢዎችን መሳሪያዎችን ለመግዛት የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ።

  • ሎት1 የህክምና እቃዎች 700 ብር
  • ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ 8000 ብር
  • ሎት 3 ህትመት 4500 ብር
  • ሎት4 የተለያዩ ጥገናዎች 8000 ብር
  • ሎት 5 የደንብ ልብስ ጨርቅና የደንብ ልብስ ስፌት 6000
  • ሎት 6 የጽዳት እቃዎች 1000 ብር
  • ሎት7  ቋሚ እቃ 7320  ብር
  • ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ 1000 ብር
  • ሎት 9 ልዩልዩ መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች መሳሪያዎች 50,000.00 ብር
  • ሎት 10 የሚወገዱ ንብረቶች 1000 ብር

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ሎቶችን ብቃት ያላቸው እና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ መ/ቤቱ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡በመሆኑም በዚህ መሰረት፣

በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑ ግብር የከፈሉ በመንግስት ግን ኤስ ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (Cpo) ከጨረታው ለነዳቸው ጋር የጨረታውን
  • አጠቃላይ ድምር 1% በማስያዝ በተለየ ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን 1 ኦሪጅናል እና 1 ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት  እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናቶች በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ቢሮ 302 በምመጣት።
  • የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ 4ኛፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ የሰራ ሰዓት ይከፈታል።
  • በተጨማሪም መ/ቤቱ ባዘጋጀው ኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የፍላጎት መግለጫ ላይ ዋጋው በትክክል ያለ ስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ እንዲሞላ በማድረግ ተጫራቾች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር በመደመር ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  • በጨረታ መክፈቻ ላይ የዘገየ ተጫራች በውድድሩ ተቀባይነት የለውም።
  • አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈጻሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የመ/ቤቱ ቁጥር 0115150015/0115150083

አድራሻችን፡ ከፍተኛ ፍ/ቤት በሄለን ህንጻ በሚወስደው አስፋልት በቤኬር ህንጻ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ

በልደታ ክ/ከተማ የህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ