በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 01, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በን/////ወረዳ 07 አስተዳደር 2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግዥ መለያ ቁጥር 01/2018 ማለትም

  • ሎት 01 ደንብ ልብስ፣
  • ሎት 02 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
  • ሎት 03 የፅዳት እቃ
  • ሎት 04 የህትመት አገልግሎቶች፣
  • ሎት 05 የመስተንግዶ አገልግሎት፣
  • ሎት 06 የቢሮ እቃዎች ጥገና አገልግሎት፣
  • ሎት 7 የትራንስፖርት አገልግሎት፣
  • ሎት 8 የጉልበትና ጭነት አውራጅና ጫኝ አገልግሎት በመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡

ለሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ለሎት 02. ብር 36,000 (ሰላሳ ስድስት ሺህ ብር) ለሎት 03 ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ለሎት 04 ብር 19,000 (አስራ ዘጠኝ ሺህ ብር) ለሎት 05. ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለሎት 06 ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ ለየብቻ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

በዚህም መሰረት፡– 

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው ፡፡
  2. የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ማህተም ማድረግ አለባቸው፤ እንዲሁም ፖስታዎች በእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በላያቸው ላይ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ፋይናንስ /ቤት 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 1130 ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል ፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ኦርጅናል ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ሎት ላይ በማስገባት በግዥ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 01 ለሎት 2 ለሎት 3 እና ለሎት 4 ናሙና ማቅረብ አለባቸው ፡፡ እንዲሁም ለሎት 5 6 7 8 በቀረበው ፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብቻ በባንክ በተረጋገጠ አሰርቶ መምጣት አለበት፡፡

አድራሻ በን///// ወረዳ 07 አስተዳደር ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ካዲስኮ አዋሽ ባንክ ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ:: ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118886532/0118885787 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ /ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር /ቤት