Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
1ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ፣
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ተጫራቾች ከዘህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
ሎት ቁጥር
|
የሎት ዝርዝር
|
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር |
ሎት1 |
የደንብ ልብስ
|
ብር 40,000
|
ሎት2 |
አላቂ የቢሮ እቃዎች
|
ብር 29,400
|
ሎት3 |
አላቂ የትምህርት እቃዎች
|
ብር 36,000
|
ሎት4 |
የሕትመት ሥራዎች
|
ብር 6,000
|
ሎት5 |
የጽዳት እቃ
|
ብር 30,000
|
ሎት6 |
ቋሚ የቢሮ እቃዎች
|
ብር 30,000
|
ሎት7 |
ሕንፃና ቁሳቁስ ጥገና እቃዎች
|
ብር 3,000
|
ሎት8 |
ፕላንትና ማሽነሪ እቃዎች
|
ብር 3,000
|
ሎት9 |
አላቂ የሕክምና እቃዎች
|
ብር 2,000
|
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 04 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
8. ጨረታው በ10ኛው ቀን በዕለቱ 10፡00 ታሽጎ 10፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
10.ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ለማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው::
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡– ከቦሌ ድልድይ 400 ሜትር ገባ ብሎ ቦሌ ሆምስ ፊት ለፊት ስልክ፦ 011 8 21 77 36 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት