Your cart is currently empty!
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 03/ት/ፅ/ቤት የፈለገ ህይወት የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ ልዩ ልዩ አስፈላጊ የሚሆኑ ማቴሪያሎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 001 2018
በአዲስ ከተማ ከ ከተማ በወረዳ 03/ት/ፅ/ቤት የፈለገ ህይወት የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ ልዩ ልዩ አስፈላጊ የሚሆኑ ማቴሪያሎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የስራ ልብስ እና የስራ ልብስ ስፌት፣
- ሎት2. አላቂ የቢሮ እቃዎችና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
- ሎት3, አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 4. አላቂ የትምህርት እቃዎችና አላቂ የህክምና እቃዎች፣
- ሎት5 ቋሚ እቃዎች (የአይቲ እቃዎችና የቢሮ እቃዎች)፣
- ሎት6. የህትመት ስራዎች እና የቢሮ ማስዋቢያ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች)፣
- ሎት7, የተለያዩ ጥናዎች ስራዎች (የማሽነሪ ጥገና አይቲ እቃዎችና የቢሮ እቃዎች)፣
- ሎት 8. ለትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ሜዳ ለመስራት እና ጊቢ ውስጥ የተለያዩ ጥገናዎች ስራ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ሎቶችና የጨረታ ኮዶች ላይ መወዳደር ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች (አመልካቾች )ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይፈልጋሉ።
ተ.ቁ
|
የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መግለጫ |
የግዥው ምድብ
|
የግዥው ሎት ምድብ
|
ምድብ ፋይናንስ መደብ
|
የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ መጠን ብር
|
1 |
የስራ ልብስ እና የስራ ልብስ ስፌት
|
ዕቃ
|
ሎት1 |
መደበኛ በጀት
|
7,000.00 0.50%
|
2 |
አላቂ የቢሮ እቃዎችና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
|
ዕቃ
|
ሎት2 |
መደበኛ በጀት
|
4,500.00 0.50%
|
3 |
አላቂ የፅዳት እቃዎች
|
ዕቃ
|
ሎት3 |
መደበኛ በጀት
|
4,875.00 0.50%
|
4 |
አላቂ የትምህርት እቃዎችና አላቂ የህክምና እቃዎች
|
ዕቃ
|
ሎት4 |
መደበኛ በጀት
|
5,800.00 1%
|
5 |
ቋሚ እቃዎች /የአይቲ እቃዎችና የቢሮ እቃዎች/
|
ዕቃ
|
ሎት5 |
መደበኛ በጀት
|
9,000.00 2%
|
6 |
የህትመት ስራዎች እና የቢሮ ማስዋቢያ እቃዎች/ ልዩ ልዩ እቃዎች
|
አገልግሎት
|
ሎት6 |
መደበኛ በጀትና ከውስጥ ገቢ
|
7,000.00 1%
|
7 |
የተለያዩ ጥገና ስራዎች የማሽነሪ ጥገና አይቲ እቃዎችና የቢሮ እቃዎች/
|
አገልግሎት
|
ሎት7 |
መደበኛ በጀትና ከውስጥ ገቢ
|
4,000.00 1%
|
8 |
ለትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ሜዳ ለመስራት እና ጊቢ ውስጥ የተለያዩ ጥገናዎች ስራ
|
አገልግሎት
|
ሎት8 |
ከውስጥ ገቢ
|
10,000.00 1%
|
1. በዘርፉ ህጋዊ ታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ክሊራንስ እና ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡ በአቅራቢ ሊስት መመዝገባቸውን /ዌብ ሳይት/ ድርጅት ዝርዝር የተመዘገቡ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ግዥ ከፍል በቀጥታ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በራሳችሁ የምታመርቱት ምርት ብቻ ደብዳቤ በመያዝ መሳተፍ እንጂ ለሌሎች እቃዎች ላይ ለምትወዳደሩበት እቃዎች እንደማንኛውም ተጫራች ማስያዥና የጨረታ ሰነድ ገዝታቹሁ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን፡፡
4. በጨረታው ላይ ለምትወዳደሩባቸው እቃዎች የእቃዎቹን ናሙና ጨርቅ በጣቃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ፡፡ ሻጭ ድርጅት ለሚያቀርቡት ዕቃ ህጋዊ ዋስትና ለአንድ ዓመት ጋራንቲ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነዳቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግ በታሸገ ፖስታ ስምና ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተብ እና ሙሉ አድራሻ በመግለፅ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል። ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለፅው ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች አለመገኘት ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን አያስተጓጉለውም። በተጫራቾች መሙላት ያለበት ከፍል መሞላት ይኖርበታል፡፡
7. አሸናፊ ተጫራቾች ውሉን ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ)ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. የጨረታ አሸናፊው በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሑፍ በተገለፀ በ7ቀናት ውስጥ ውሉን መዋዋል ይጠበቅበታል።
አድራሻ፡– ከሰባተኛ ወደ አብነት የሚወስደው መንገድ አዲስ ከተማ ክ/ከ በወረዳ 03 ባለው ቅያስ ውስጥ ገባ ብሎ
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 03/ት/ፅ/ቤት
የፈለገ ህይወት የመ/ደ/ት/ቤት