በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ እና እኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ለቢሮ መገልገያ የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፤ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች፤ የሞተር ሳይክል ጎማዎች፤ የቢሮ ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 01, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ እና እኮኖሚ ትብብር /ቤት 2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ለቢሮ መገልገያ የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፤ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች፤ የሞተር ሳይክል ጎማዎች፤ የቢሮ ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. 2017 የመንግስት ግብር መክፈላቸዉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ እና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች ከፈዴራል ወይም ከክልል ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸዉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የተ..(VAT)ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና 2 % ለመንግስት ለመቁረጥ ፍቃደኛ የሆኑና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN Number ) የላቸው ሆኖ ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች መስሪያ ቤቱ በሚያወጣው መመሪያ መስፈርት ግዴታ መወጣት አለበት፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ፦

  • ለጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችብር 17,000.00 (አስራ ሰባት ሺህ)
  • ለሰራተኞች የደንብ ልብስብር 5,000.00 ( አምስት ሺህ)
  • ለኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችብር 20,000.00 ( ሃያ ሺህ)
  • ለቢሮ ፈርኒቸሮችብር 8,000.00 ( ስምንት ሺህ)
  • ለግንባታ ለሚዉሉ መሳሪያዎችብር 5,000.00 (አምስት ሺህ)
  • የተለያዩ የመኪና የሞተር ሳይክል ጎማዎችብር 14,000.00 ( አስራ አራት ሺህ)
  • በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቂረቢያ ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሽገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. የጨረታው ሰነድ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት በእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (በአስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ቀን 230 -1130 ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡

8. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫት (VAT/ 15%) ያካተተ መሆን አለበት፡፡

9, ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ያስቀመጥነው የዕቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ መጨመር እና መቀነስም ይቻላል፡፡

11. ተጫራቾች ተወዳድረዉ ያሸነፉበትን የቢሮ ፈሪኒቸሮችን(Furniture)ገጥመዉ ማስረከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

12. ጨረታዉ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው የስራ ቀን 16 ኛው የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግተው በዕለቱ 430 በአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ላይ ባይገኙም ጨረታዉን ከመክፈት አያግድም፡፡

13 ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች እስከ አቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ድርስ በራሳቸው ወጪ ትራንስፖርት ያቀርባሉ፡፡

14. ተጫራቾች ዕቃዎቹን የሚያስረክቡበት በቱሉ ዋዩ ከተማ አቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ / ቤት ንብረት ክፍል ሆኖ አሸናፍዎቹ በተዋዋሉበት ውል መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡

ስልክ ቁጥር 0910266687/0913407800 ደውለው መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

 በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የአቤ ደንጎሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት